አትጠራጠረው (Ateteraterew) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)

ርዝመት (Len.): 3:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው

ከጠላት ፡ ፍላፃ ፡ ከሰይፍ ፡ ያድንሃል
በረህብም ፡ ዘመን ፡ ከሞት ፡ ያስጥልሃል
ስሙን ፡ ያስከብራል ፡ ቁም ፡ ነገርን ፡ ያውቃል
ሕጻን ፡ ስላይደለ ፡ ያለውን ፡ ይፈጽማል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው

በታማንነቱ ፡ ተው ፡ ገደብ ፡ አትስጠው
ለወላዋይነትህ ፡ ፅናት ፡ አትንፈገው
የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይዋሽም
የገባልህን ፡ ቃል ፡ ፈፅሞ ፡ አይክድም

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው

ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እስከሆንክ ፡ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ ነው
አውጥቶ ፡ እንዳይጥልህ ፡ ብቻ ፡ አትተወው
አስብ ፡ ቆም ፡ ብለህ ፡ ያሳለፍከውን ፡ ዘመን
ዛሬም ፡ አምነህ ፡ ጥራ ፡ ያኔ ፡ ያዳነህን

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው

ስሙን ፡ እየጠራህ ፡ ስንቱን፡ አምልጠሃል
ከስንቱስ ፡ አደጋ ፡ ስንት ፡ ጊዜ ፡ ድነሃል
ውለታውን ፡ ሲረሱ ፡ ጌታ ፡ ቅር ፡ ይለዋል
በቃሉ ፡ ብታምን ፡ ሁሉ ፡ ይቻልሃል

አዝ፦ ኢየሱስን ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ አትጠራጠረው
መዋሸት ፡ አያውቅም ፡ ተስፋህን ፡ ጠብቀው
አይጥልህምና ፡ በመከራ ፡ ጥራው
አፍህ ፡ አያመነው ፡ በልብህ ፡ አትግታው