ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ (Gieta Yesus Atetewegn) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 3:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ኃጢአት ፡ በዛብኝ ፡ ጉልበቴም ፡ ደከመ
መራመድ ፡ አልቻልኩም ፡ መንገዴም ፡ ጨለመ
ጠላቴም ፡ ይህን ፡ ሲያይ ፡ ሊሰብረኝ ፡ አለመ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
መጥተህ ፡ አውጣኝ

አንተን ፡ እያሳዘንኩ ፡ ደምህን ፡ እየረገምኩ
ለልጆችህ ፡ ደግሞ ፡ እንቅፋት ፡ እየሆንኩ
መላው ፡ ጠፋኝ ፡ ጌታ ፡ ግራ ፡ ተጋባሁኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
መጥተህ ፡ አውጣኝ

ቃልህን ፡ እንዳላነብ ፡ ፍላጐቴ ፡ ከድቶኝ
ደግሞም ፡ እንዳልፀልይ ፡ ድካም ፡ ተጫጭኖኝ
በጣሙን ፡ ዝያለሁ ፡ ተጐሳቁያለሁ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
መጥተህ ፡ አውጣኝ

በቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ሕይወቴ ፡ ታትሞ
በልጆችህ ፡ መሃል ፡ የእኔ ፡ መኖር ፡ ጠቅሞ
ልገናኝህ ፡ አብቃኝ ፡ ሁሉ ፡ ተፈጽሞ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
መጥተህ ፡ አውጣኝ

መውደቅ ፡ በጥቂቱ ፡ መሞት ፡ በጥቂቱ
መሆኑን ፡ አይቻለሁ ፡ ከመውደቅ ፡ ጠብቀኝ
ማዕበሉ ፡ እንዳይጥለኝ ፡ ጐርፉም ፡ እንዳይወስደኝ

አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ አትተወኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አትልቀቀኝ
በጭንቀት ፡ ታስሬ ፡ እያለሁ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ
መጥተህ ፡ አውጣኝ