From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ (Tesfaye Gabisso)
|
|
፯ (7)
|
አልበም (ያይሃል (Yayehal) (Vol. 7))
|
ቁጥር (Track):
|
፬ (4)
|
ርዝመት (Len.):
|
4:17
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Gabisso)
|
|
አዝ፦ ቃሉን ፡ ከቶ ፡ የማያጥፍ
ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የነገረንን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽሞት ፡ አይተናልና
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናደርገዋለን ፡ በምሥጋና
የኃጢአትን ፡ ከተማ ፣ የዲያብሎስን ፡ ሥራ
ሲያፈራርሰው ፡ አይተናል ፡ ያን ፡ ምሽግ ፡ ያንን ፡ ተራራ
ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ተገልጦ ፣ የሕይወታችን ፡ ብርሃን
የተስፋ ፡ ቃሉን ፡ ፈጸመው ፡ በሞቱ ፡ እኛን ፡ በማዳን
አዝ፦ ቃሉን ፡ ከቶ ፡ የማያጥፍ
ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የነገረንን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽሞት ፡ አይተናልና
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናደርገዋለን ፡ በምሥጋና
በሰላምና ፡ በሕይወት ፣ በበጐ ፡ ነገርም ፡ ምክር
አበሳችን ፡ እንዲወገድ ፣ እሮሮአችንም ፡ እንዲቀር
በእኛ ፡ ያለውን ፡ ነገር ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ አይቶ
ቀንበራችንን ፡ ሰበረው ፡ ለቅሶአችንን ፡ እርሱ ፡ ሰምቶ
አዝ፦ ቃሉን ፡ ከቶ ፡ የማያጥፍ
ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የነገረንን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽሞት ፡ አይተናልና
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናደርገዋለን ፡ በምሥጋና
የሲኦልን ፡ ማስፈራራት ፣ የመከራን ፡ አውሎ ፡ ነፋስ
የኃያላኑን ፡ ጭካኔ ፣ የቁጣቸውን ፡ እስትንፋስ
የማዕበሉን ፡ ሁሉ ፡ ጩኸት ፣ የዓመጽንም ፡ ዝማሬ
በሥልጣኑ ፡ ቃል ፡ ገስጾ ፡ ዝም ፡ አሰኝቶታል ፡ ዛሬ
አዝ፦ ቃሉን ፡ ከቶ ፡ የማያጥፍ
ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የነገረንን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽሞት ፡ አይተናልና
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናደርገዋለን ፡ በምሥጋና
የመማጸኛ ፡ ግንብ ፡ ነው ፣ የድሆች ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ
ምቹ ፡ መሸሸጊያ ፡ ዓለት ፡ የለንም ፡ ከኢየሱስ ፡ ወዲያ
ብዙዎቹም ፡ ይድናሉ ፡ ገብተው ፡ ከዚህ ፡ መጠለያ
ስለሚሆንልን ፡ ሁሉ ፡ ይክበር ፡ ጌታ ፣ ሃሌሉያ!
አዝ፦ ቃሉን ፡ ከቶ ፡ የማያጥፍ
ታማኝ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የነገረንን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽሞት ፡ አይተናልና
ከፍ ፡ ከፍ ፡ እናደርገዋለን ፡ በምሥጋና
|