From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
ይህ ፡ ጽሑፍ ፡ ገና ፡ አልተረጋገጠም ። እርማቶች ፡ ሊያስፈልጉት ፡ ይችላል ። ከቻሉ ፡ እርስዎ ፡ ያሻሽሉት ።
|
ምህረቱ አያልቅምና ለዘላለም ቸር ነዉና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጎበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና አቅርቡለት
በእለልታ ስገዱለት፡፡
በባቢሎን ወንዞች ማዶ አዝነን ተቀምጠን
ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ እጅግ አለቀስን
የመጽናናት አምላክ ከላይ ግን ያየናል
እንባችንን ጠርጎ ስብራታችንን ይጠግንልናል፡፡
ምህረቱ አያልቅምና ለዘላለም ቸር ነዉና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጎበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና አቅርቡለት
በእለልታ ስገዱለት፡፡
የችግረኞችን ጩኸት ሰምቶ አይጨክንም
ምርጦችን ከልቡ በፍጹም አያስጨንቅም
ጠላታቸዉን ሊበትን በነጎድጓድ አንቀጥቅጦ
ረድኤታቸዉ ከተፍ ይላል ከሰማያት በ ግርማዉ ተገልጾ፡፡
ምህረቱ አያልቅምና ለዘላለም ቸር ነዉና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጎበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና አቅርቡለት
በእለልታ ስገዱለት፡፡
በሥጋዎቻቸዉ የገነኑ ፈጽመዉ ሲወድቁ
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ
በእንባቸዉ ፍሬ እያሸበረቁ
በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ ይከብራሉ እንደ እንቁ፡፡
ምህረቱ አያልቅምና ለዘላለም ቸር ነዉና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጎበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና አቅርቡለት
በእለልታ ስገዱለት፡፡
ለእኛ መጠጊያች ጌታ እግዚአብሔራችን ነዉ
በምንም አንፈራም እርሱ ኃይላችን ነዉ
ከሰይጣ አሽክላ ስሙ ይጠብቀናል
ለአሞራም ሳይሰጠን በክንፎቹ አዝሎ ቤቱ ያገባናል፡፡
ምህረቱ አያልቅምና ለዘላለም ቸር ነዉና
የማዳን ኃይሉን ላሳየን በክንዱ ለሚጎበኘን
መልካሙን መዓዛ በምስጋና አቅርቡለት
በእለልታ ስገዱለት፡፡
|