From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው ፡ በሥጋም ፡ አይደፈር
እጅግም ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ በሰው ፡ የማይገመት
ዛሬም ፡ እንደቀድሞው ፡ ክንዱ ፡ ኃያል ፡ ያደርጋል
ቢወዱም ፡ ቢጠሉም ፡ ኢየሱስ ፡ ይነግሣል
አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሥሙን ፡ በመታመን ፡ ሲቀርቡት ፡ ይቀርባል
በደከመች ፡ ሕይወት ፡ ብርታት ፡ ይጨምራል
ሞገዱን ፡ ፀጥ ፡ አድርጐ ፡ ሰላምን ፡ ይሰጣል
ምንጩን ፡ አጠጥቶ ፡ በረሃን ፡ ያለማል
አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የማይታየው ፡ ባህሪ ፡ የዘላለም ፡ ኃይሉ
በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ በእውነት ፡ ሲያስተውሉ
ከጥንትም ፡ ጀምሮ ፡ ከተሰሩት ፡ ደምቆ
ይኖራል ፡ ኢየሱስ ፡ ህልውናው ፡ ታውቆ
አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የተዓምራት ፡ አምላክ ፡ ክንዱ ፡ መች ፡ አጠረ
ሰው ፡ ያወቀ ፡ መስሎት ፡ ብዙ ፡ የመረመረ
ኃጢአትን ፡ አጣጥሞ ፡ ለፍርድ ፡ እየኖረ
ጌታን ፡ የለም ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ አጣመረ
አዝ፦ በሰማይ ፡ በምድርም ፡ ሙሉ ፡ ስልጣን ፡ ያለው
የሚለውጥህ ፡ እንጂ ፡ የማይለውጠው
አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ማለት ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
|