እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው (Ene Negn Teraraw) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(3)

ክርስቲያን ፡ ተሻገረ
(Christian Teshagere)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 2:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

የምድረ ፡ በዳው ፡ ድምጽ ፡ የአዋጅ ፡ ነጋሪው ፡ ቃል
መንገዱን ፡ ጥረጉ ፡ አስተካክሉ ፡ ይላል
ክብሩ ፡ ይገለጣል ፡ ኮረብታው ፡ ዝቅ ፡ ይበል
ሥጋ ፡ ለባሽ ፡ ሁሉ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ያያል

አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት
የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት
ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ

ጌታ ፡ ትዕቢተኛውን ፡ እጅግ ፡ ይቃወማል
ለትሁታኑ ፡ ግን ፡ ፀጋውን ፡ ይሰጣል
ለስም ፡ አገልጋይ ፡ ነኝ ፡ ፀጋ ፡ ግን ፡ ያንሰኛል
የእኔ ፡ ዝና ፡ ወጥቶ ፡ የአንተ ፡ ተሰውሯል

አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት
የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት
ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ

ኦ ፡ ምን ፡ ይሻለኛል ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቶሎ ፡ ና
ሰዎች ፡ አንተን ፡ ሊያይ ፡ ከቶ ፡ አልቻሉምና
የልቤን ፡ ኮረብታ ፡ ተራራውን ፡ ናደው
ፍሬም ፡ እንዲመጣ ፡ ቅንጣቱን ፡ ግደለው

አዝ፦ እኔ ፡ ነኝ ፡ ተራራው ፡ ትልቁ ፡ እንቅፋት
የሕዝብህ ፡ ጉስቁልና ፡ የድካሙ ፡ ምክንያት
ኦ ፡ ምንኛ ፡ ይመራል ፡ የትዕቢቱ ፡ ፅዋ
ጌታ ፡ ሆይ ፡ ዝቅ ፡ አርገኝ ፡ ሳይገለኝ ፡ ፍሬዋ