From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የጽድቅ ፡ ሥራህን ፡ ጌታ ፡ ሰራህና
በጨለማ ፡ ላሉ ፡ ፀሐይ ፡ ወጣችና
ከዘለዓለም ፡ ጥፋት ፡ አንተ ፡ ያዳንካቸው
በታዳጊነትህ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አላቸው (፪x)
አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ
ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ
ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ
የመስቀል ፡ ፍቅርህን ፡ ለሰው ፡ ይነግራሉ
የቅድስናህን ፡ ክብር ፡ ያወራሉ
በክንፎችህ ፡ ጥላ ፡ ታምነው ፡ ይኖራሉ
የማዳን ፡ ክንድህን ፡ ሁልጊዜ ፡ ያያሉ (፪x)
አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ
ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ
ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ
ከሥም ፡ ሁሉ ፡ በላይ ፡ ሥምህ ፡ የከበረ
ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ያማረ
የሚመስልህ ፡ የለም ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነህ
ከፍ ፡ ብለህ ፡ ንገሥ ፡ ግርማ ፡ ተሞልተህ (፪x)
አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ
ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ
ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ
ክብርህ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ይታይ ፡ አምላካችን
ምላስም ፡ ይመስክር ፡ ታላቅነትህን
በሰማይ ፡ በምድር ፡ ትሰለጥናለህ
ሁሉም ፡ ከእግርህ ፡ በታች ፡ አንተ ፡ ትገዛለህ (፪x)
አዝ፦ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ያለህ ፡ የነበርህ
ትልቁን ፡ ኃይልህን ፡ ለብሰህ ፡ የከበርህ
ሥምህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ይመስገን ፡ ይባረክ
ጉልበት ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ይንበርከክ (፫x)
|