From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ
በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
ለተጨነቀ ፡ ልቡ ፡ እረፍት ፡ አግኝቶ
ጉዞውን ፡ ቢጀምር ፡ ወደ ፡ ሰማያዊ ፡ አገር ፡ አቅንቶ
ሰይጣን ፡ በተንኮል ፡ በወጥመዱ ፡ አጥሮ ፡ መንገድ ፡ ቢዘጋበት
ጌታም ፡ ይህን ፡ አይቶ ፡ ወጥመዱን ፡ ሰባብሮ ፡ በሩን ፡ ከፈተለት
አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ ፡
በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
መዋጋትን ፡ እንዲለምድ ፡ ሸለቆ ፡ ወርዶ
ከቤት ፡ ከንብረቱ ፡ ከነፍሱ ፡ አብልጦ ፡ ጌታውን ፡ ወዶ
ሰልፉ ፡ በረታና ፡ ክፉኛ ፡ ተጠቅቶ ፡ እጅና ፡ እግሩ ፡ ዝሎ
ኢየሱስ ፡ ደርሶለት ፡ ድልን ፡ አወጀለት ፡ ባላንጣውን ፡ ጥሎ
አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ
በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ
እጆቹን ፡ በእርፉ ፡ ላይ ፡ አንዴ ፡ አሳርፏል
ወደኋላ ፡ ማየት ፡ ነውር ፡ በመሆኑ ፡ ሥራውን ፡ ቀጥሏል
እምነት ፡ ሳይጓደል ፡ አደራ ፡ ሳይበላሽ ፡ ተጠንቅቆ ፡ ታግሎ
እፎይ ፡ ማለቱ ፡ ነው ፡ በክብር ፡ ተራራ ፡ አክሊል ፡ ተቀብሎ
አዝ፦ በወንጌል ፡ እውነት ፡ ወገቡን ፡ ታጥቆ
ስለ ፡ ሕይወት ፡ ቃል ፡ ጸንቶ ፡ ተዋድቆ
በጌታ ፡ ብርታት ፡ የከበበውን ፡ ጭፍራ ፡ ሰንጥቆ
በጐ ፡ ወታደር ፡ በድል ፡ አለፈ ፡ ያንን ፡ የሞትን ፡ ሸለቆ (፪x)
|