From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የመከራ ፡ እቶን ፡ የማንጠሪያ ፡ እሳት
የመፈተኛ ፡ ፍም ፡ የመመዘኛ ፡ ጣት
ነበር ፡ በጀግኖች ፡ ዘንድ ፡ ባለፉት ፡ ጦረኞች
ባለፉበት ፡ መንገድ ፡ የድል ፡ ባለቤቶች
አዝ፦ ለእኔም ፡ ያንን ፡ ፀጋ ፡ በሕይወቴ ፡ አምቄ
በችግሬ ፡ ሰዓት ፡ ጌታዬን ፡ ጠብቄ
ልደርስ ፡ እወዳለሁ ፡ ወደዚያ ፡ ደረጃ
በሚሰጠኝ ፡ ጉልበት ፡ በእምነት ፡ እርምጃ
በቀደመው ፡ ትውልድ ፡ እሳት ፡ ነበር ፡ ልኩ
ለእምነት ፡ ትጋዳዮች ፡ የትግል ፡ መድረኩ
ለማይጠፋው ፡ ክብር ፡ ለሕያውም ፡ ተስፋ
ተዋግተው ፡ አልፈዋል ፡ በትልቅ ፡ ነቀፋ
አዝ፦ ለእኔም ፡ ያንን ፡ ፀጋ ፡ በሕይወቴ ፡ አምቄ
በችግሬ ፡ ሰዓት ፡ ጌታዬን ፡ ጠብቄ
ልደርስ ፡ እወዳለሁ ፡ ወደዚያ ፡ ደረጃ
በሚሰጠኝ ፡ ጉልበት ፡ በእምነት ፡ እርምጃ
አምላካቸው ፡ ከብሯል ፡ በአምልኮ ፡ ስግደት
በትልቅ ፡ ተጋድሎ ፡ በወንጌል ፡ ጤንነት
ከብረው ፡ አስከብረው ፡ የሕይወታቸውን ፡ ጌታ
ሊገናኙት ፡ ወጡ ፡ ያንን ፡ ባለ ፡ ውለታ
አዝ፦ ለእኔም ፡ ያንን ፡ ፀጋ ፡ በሕይወቴ ፡ አምቄ
በችግሬ ፡ ሰዓት ፡ ጌታዬን ፡ ጠብቄ
ልደርስ ፡ እወዳለሁ ፡ ወደዚያ ፡ ደረጃ
በሚሰጠኝ ፡ ጉልበት ፡ በእምነት ፡ እርምጃ
እኛም ፡ ተጠርተናል ፡ እንምሰል ፡ እነርሱን
የመከራን ፡ እሳት ፡ እንድናየው ፡ ልኩን
ስለዚህ ፡ ተጋደል ፡ የወንጌል ፡ አርበኛ
ሠይጣንን ፡ ግጠመው ፡ ያንተን ፡ ወደረኛ
ነው-ና- ፡ ድል ፡ የእኛ
አዝ፦ ለእኔም ፡ ያንን ፡ ፀጋ ፡ በሕይወቴ ፡ አምቄ
በችግሬ ፡ ሰዓት ፡ ጌታዬን ፡ ጠብቄ
ልደርስ ፡ እወዳለሁ ፡ ወደዚያ ፡ ደረጃ
በሚሰጠኝ ፡ ጉልበት ፡ በእምነት ፡ እርምጃ
|