መድኃኒታችን (Medhanitachen) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(10)

አዎን ፡ ይሆናል
(Awon Yehonal)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፬ (2012)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ በመውደዱ
በዘለዓለም ፡ ምክሩ ፡ በበጐ ፡ ፈቃዱ
ውድ ፡ ልጁን ፡ ልኮ ፡ ከኃጥያት ፡ አዳነን
ገንዘቡም ፡ ሊያደርገን ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ዋጀን

መድኃኒታችን ፡ ከአመፅ ፡ ተቤዠን
በደሙ ፡ አንጽቶ ፡ ለእራሱ ፡ ቀደሰን
የመንግሥቱም ፡ ወራሽ ፡ ወገን ፡ አደረገን

የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ በፀጋ ፡ ተሞልቶ
የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በኃይል ፡ ተቀብቶ
ሕዝቡን ፡ እየፈታ ፡ ዞረ ፡ እየፈወሰ
የዲያቢሎስንም ፡ ሥራ ፡ እያፈረሰ

የአምላካችን ፡ ማዳን ፡ የታዳጊነቱ
ዝናውም ፡ ሲነገር ፡ የኃያልነቱ
ጠላት ፡ተቀጥፈዋል፡ ነደደ:መኣቱ።

ሊቀ ፡ ካህናቱ ፡ የአይሁድም ፡ አለቆች
ሄሮድስ ፡ ጲላጦስ ፡ የዛ ፡ ዘመን ፡ ዳኞች
ቢመረምሩትም ፡ በደል ፡ አጡበት
ጻድቅ ፡ ነው ፡ ጌታችን ፡ የለውም ፡ ስህተት

ነውርና ፡ እድፍ ፡ ነቀፋ ፡ የሌለው
መስዋዕት ፡ በመሆን ፡ ስለ ፡ እኛ ፡ የሞተው
ቅዱስ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ጀርባውን ፡ በጅራፍ ፡ በእጅጉ ፡ ገርፈው
እጆቹን ፡ እግሮቹን ፡ በምስማር ፡ ቸንክረው
በመስቀል ፡ አዋሉት ፡ እንደ ፡ በደለኛ
የነፍሳቸውን ፡ ዋስ ፡ ያን ፡ ታማኝ ፡ እረኛ

የሚያደርጉትን ፡ ባለማወቃቸው
አብ ፡ ኃጥያታቸውን ፡ እንዳይዝባቸው
እርሱ ፡ ግን ፡ ማለደ ፡ ይቅር ፡ እንዲላቸው

መተላለፋችን ፡ ተግሳጽ ፡ ውጣታችን
ደዌ ፡ ህመማችን ፡ ስቃይ ፡ መከራችን
በምህረቱ ፡ አዋጅ ፡ ወደቀ ፡ ከእዳችን
በኢየሱስ ፡ ቤዛነት ፡ ተሻረ ፡ ሞታችን

በእርሱ ፡ ስላገኘን ፡ ሰላምና ፡ እርካታ
ሃዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታን ፡ በዕልልታ
ስለ ፡ ለወጠልን ፡ ይክበር ፡ የእኛ ፡ ጌታ

በአንተ ፡ ስላገኘን ፡ ሰላምና ፡ እርካታ
ሃዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታን ፡ በዕልልታ
ስለ ፡ ለወጥክልን ፡ ይክበር ፡ የእኛ ፡ ጌታ