From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
በልጅህ ፡ ደም ፡ "ሕይወት ፡ ሰላም ፡ ይሁን!" ፡ ብለህ
ለሐጢአታችን ፡ ይቅርታን ፡ አውጀህ
እግዚአብሔር ፡ ሆይ! ፡ ታረቅኸን ፡ ተመስገን
የክብርህ ፡ ማረፊያ ፡ መቅደስህ ፡ አደረግኸን (፪x)
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
ዙፋንህ ፡ በሰማይ ፡ የሆነ ፡ ንጉሥ
በምድር ፡ በእኛ ፡ መሃል ፡ ስምህ ፡ ይቀደስ
የመዓዛ ፡ ሽታ ፡ መሥዋዕታችንን
ምሥጋናን ፡ ተቀበል ፡ ከሕይወታችን (፪x)
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
ቅዱስ! ፡ ቅዱስ! ፡ ቅዱስ! ፡ እያሉ ፡ መላዕክት
በትጋት ፡ ሲያመልኩህ ፡ ቀንም ፡ ሆነ ፡ ሌሊት
ከእኛም ፡ ይድረስህ ፡ ውዳሴ ፡ ማሕሌት
ምልጃም ፡ ጸሎታችን ፣ ምሥጋና ፡ ስግደት (፪x)
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
መቅረዝህም ፡ ይንደድ ፣ ይታይ ፡ ብርሃንህ
የጸሎት ፡ ቤትህን ፡ ሙላው ፡ በክብርህ
አሕዛብም ፡ ይምጡ ፡ ወደ ፡ ጸዳልህ
ይስገዱልህ ፡ ድነው ፡ በቅዱስ ፡ ስምህ (፪x)
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
የዓለም ፡ ገበያ ፡ እንዳይሆን ፡ ማትረፊያ
ቀድሰህ ፡ ጠብቀው ፡ የአንተን ፡ ማደሪያ
የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ፈውስን ፡ መቀበያ
ይሁንልን ፡ ቤትህ ፡ የመንፈስ ፡ መኖሪያ (፪x)
አዝ፦ የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ጌታ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ
የጸሎት ፡ ቤት ፡ ይሁን ፡ ኢየሱስ ፣ ይኸ ፡ መቅደስህ (፪x)
|