From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
የፀጋ ፡ የምህረት ፡ ዘመኑ ፡ አብቅቶ
ብርሃን ፡ ተሰውሮ ፡ የጥሪው ፡ ቀን ፡ መሽቶ
ሰማያት ፡ ተፈተው ፡ ምድር ፡ ሳትናውጥ
በነበልባል ፡ እሳት ፡ ጌታም ፡ ሳይገለጥ
አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ
ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ
ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም
አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም
አብሮ ፡ ደስ ፡ ይበለን ፡ ትንሽ ፡ ቆይ ፡ ስትልህ
ዓለም ፡ በለዘብታ ፡ እያባበለችህ
ተደላ ፡ ትካዜና ፡ ቁጭትን ፡ ጠብቆ
ሲዖል ፡ እንዳትገባ ፡ ሳታስበው ፡ ከቶ
አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ
ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ
ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም
አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም
የእግዚአብሔር ፡ ነገር ፡ ለፍጥረታዊ ፡ ሰው
ሊገባው ፡ አይችልም ፡ ፍፁም ፡ ሞኝነት ፡ ነው
ፍጥረታዊውን ፡ ሥጋ ፡ መንፈሱ ፡ ሲሽረው
ያኔ ፡ ትረዳለህ ፡ መንገዱ ፡ ጥበብ ፡ ነው
አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ
ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ
ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም
አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም
በመንታ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ሆነህ ፡ ስታማርጥ
ፈጽሞ ፡ ላትረካ ፡ መንገድ ፡ ስትለዋውጥ
ሞት ፡ ጥላውን ፡ ጥሎ ፡ አፍኖ ፡ ሳይወስድህ
ጌታን ፡ ተቀበለው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የሚያረካህ
አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ
ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ
ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም
አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም
|