From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አመጻዬ ፡ ወደ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ወሰደችኝ
ውኃ ፡ በሌለው ፡ በረሃ ፡ አንከራተተችኝ
ለውድቀቴ ፡ እውቀት ፡ ትዕቢትን ፡ አስተማረችኝ
ጥማት ፡ ሲያቃጥለኝ ፣ እልህ ፡ ሲታገለኝ
እውነት ፡ ስትወርሰኝ ፣ ጥበብ ፡ ስትገስጸኝ
መንፈሱ ፡ ሲረታኝ ፣ ጌታን ፡ አገነሁት
አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ (፪x)
ሰማያዊ ፡ ጥበብ ፡ ዓይንን ፡ ትከፍታለች
ለሰነፎች ፡ ብልሃትን ፡ ታስተምራለች
ከምዝምዝ ፡ ወርቅና ፡ ከቀይ ፡ ዕንቁ ፡ ትበልጣለች
አጥብቀህ ፡ ብትሻት ፡ ብትፈላልጋት
ድምጽህን ፡ አንስተህ ፡ ጥበብን ፡ ብጠራት
ያን ፡ ጊዜ ፡ ታውቃለህ ፡ እግዚአብሔርን ፡ መፍራት
አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ (፪x)
የዚህች ፡ ዓለም ፡ መርማሪ ፡ ወዴት ፡ አለ
የዘመናትን ፡ ጥያቄ ፡ ያቃለለ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሊቁ ፡ ለእኛ ፡ የተሰቀለ
ከበረሃው ፡ መሃል ፡ ሕይወት ፡ ያፈለቀ
የሰይጣንን ፡ ስልጣን ፡ መትቶ ፡ ያደቀቀ
ለእርሱ ፡ ስንሸነፍ ፡ ጥያቄው ፡ አለቀ
አዝ፦ ጠቢብ ፡ በጥበቡ ፡ አይመካ
ኃያልም ፡ በኃይሉ ፡ አይመካ
ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እግዚአብሔር ፡ ጽድቅንና ፡ ፍርድን
በምድር ፡ ላይ ፡ ማድረጉን ፡ ያወቀ
በጌታ ፡ ይመካ (፪x)
|