From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ (Tesfaye Gabisso)
|
|
፩ (1)
|
አልበም (1)
|
ቁጥር (Track):
|
፲ ፩ (11)
|
ርዝመት (Len.):
|
3:55
|
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች (Other Songs in the Album)
|
|
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች (Albums by Tesfaye Gabisso)
|
|
እግዚአብሔር ኃያል
በሰልፉም ደግሞ ኃያል
ከቶ እስከ ዛሬ ለማን ተረቶ ያውቃል (፪
ህዝቡን ፡ ከልሎ ፡ የሚዋጋ
ለጠላት ፡ ዛቻ ፡ የማይሰጋ
ብድራትን ፡ መላሽ ፡ የእኛ ፡ አምላክ
ይርታ ፡ እንጂ ፡ መረታትን ፡ አያውቅ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ኃያል
በሰልፉም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x)
የእምነት ፡ ባለድል ፡ ሳይጸጸት
ጌታን ፡ አምኖ ፡ ሰው ፡ አያፍርበት
ለተስፋው ፡ ፈቶ ፡ ሰንሰለት
ሕይወቱን ፡ ሰጥቷል ፡ ሳትሰስት (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ኃያል
በሰልፉም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x)
አንተም ፡ በኃይሉ ፡ ድል ፡ ነስተህ
በእቶን ፡ ተፈትነህ ፡ ነጥረህ
ለመንግሥቱ ፡ ብቁ ፡ ሆነህ
እንድትወጣ ፡ ጌታ ፡ ይርዳህ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ኃያል
በሰልፉም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x)
ያን ፡ ጊዜ ፡ ተዋግቶ ፡ የረታ
የጠላቱን ፡ ጅማት ፡ የፈታ
በፅኑ ፡ አመታት ፡ የሚመታ
ሁሉን ፡ የሚችል ፡ የድል ፡ ጌታ (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ኃያል
በሰልፉም ፡ ደግሞ ፡ ኃያል
ከቶ ፡ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ለማን ፡ ተረቶ ፡ ያውቃል (፪x)
|