From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በእምነት ፡ መኖሪያዬን ፡ ሰርተው ፡ ውብ ፡ አድርገህ
ምግቤን ፡ ያለ ፡ ድካም ፡ እንድበላ ፡ ብለህ
ያስቀመጥክኝን ፡ ሰው ፡ ወረት ፡ ሲደልለኝ
ከሕይወት ፡ ጋራ ፡ ሆንከኝ ፡ በቸልታ ፡ አትየኝ
አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ
ልቤ ፡ እየቸኮለ ፡ እግሬ ፡ ሮጥ ፡ እያለ
ውርደትን ፡ ለማየት ፡ ዓይኔ ፡ እየከጀለ
ድንበር ፡ እየጣሰ ፡ ከኃጢአት ፡ እየዋለ
የማታ ፡ የማታም ፡ የዛሬ ፡ ቀን ፡ ለየ
አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ
የሙጃ ፡ ቡቃያ ፡ ፈጥኖ ፡ እየበቀለ
ፀሐይ ፡ ስትወጣ ፡ ነዶ ፡ የተቃጠለ
አስቦኛል ፡ እኔን ፡ በረከት ፡ እንዳፈራ
አንስተህ ፡ አትጣለኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አደራ
አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ
በጐልያድ ፡ ፊት ፡ ሳዖል ፡ በዓይኖችህ ፡ ተንቆ
ብላቴናው ፡ ዳዊት ፡ ተቀብቷል ፡ ልቆ
ዓይኔን ፡ ግለጠውና ፡ ስፍራዬ ፡ ልወቀው
አሳድገኝ ፡ እንጂ ፡ ዕድሜዬን ፡ አትቁረጠው
አዝ፦ ባስቀመጥከኝ ፡ ቦታ ፡ ፀንቼ ፡ እንድቆይ
መጥተህ ፡ ስትጐበኘኝ ፡ በእኔ ፡ ደስ ፡ እንዲልህ
ፀጋህን ፡ አብዛልኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ
|