From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን
የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን
ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን
የሕይወት ፡ ምርጫችን
እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x)
ከሁሉ ፡ የሚበልጠውን ፡ ተመልክተው
ከየምድሩ ፡ ጉድጓድ ፡ ተቅበዝብዘው
ነፍስን ፡ ከሚዋጋ ፡ ምኞት ፡ ርቀው
ወንዙን ፡ ተሻገሩ ፡ አሸንፈው (፫x)
አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን
የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን
ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን
የሕይወት ፡ ምርጫችን
እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x)
ቅን ፡ ከምትመስል ፡ ሰፊ ፡ መንገድ
ወጥተን ፡ በጠባቡ ፡ ስንሰደድ
በዚህ ፡ ጐዳና ፡ ላይ ፡ ሕይወት ፡ አለ
ቆርጦ ፡ ለሚከተል ፡ የታደለ (፫x)
አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን
የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን
ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን
የሕይወት ፡ ምርጫችን
እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x)
ባለ ፡ ፀጋ ፡ ሲሆን ፡ ደህይቶልን
ባለ ፡ ማዕረግ ፡ ሲሆን ፡ ተዋርዶልን
እውነተኛውን ፡ ፍቅር ፡ ገለጸልን
እኛም ፡ በእርሱ ፡ መንገድ ፡ እንሄዳለን (፫x)
አዝ፦ በእምነት ፡ ድል ፡ እየነሱ ፡ ያለፉትን
የቀደሙትን ፡ እያየን ፡ ከፊታችን
ልንቆም ፡ ያስፈልገናል ፡ ለጌታችን
የሕይወት ፡ ምርጫችን
እርሱ ፡ ነውና ፡ ዋስትናችን (፪x)
|