የባዘንከው ፡ ውድ ፡ ወንድሜ (Yebazenkew Wed Wendemie) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Tesfaye Gabisso Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

አልበም
(ምህረቱ ፡ አያልቅምና (Meheretu Ayalqemena) (Vol. 4))

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 2:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

በከንቱ ፡ ሮጠህ ፡ ጉልበትህ ፡ ባክኖ ፡ ጨርሶ ፡ አልቆ
በኃጢያት ፡ ሸክም ፡ ነፍሽ ፡ መንምና ፡ አጥንትህ ፡ ደርቆ
መድረሻህ ፡ ጠፍቶብህ ፡ ግራ ፡ ገብቶህ ፡ የምትባዝን
የዓለምን ፡ ቤዛ ፡ ቀርበህ ፡ አማክረው ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስን

አዝ፦ የባዘንከው ፡ ውድ ፡ ወንድሜ
አዳምጠኝ ፡ እስኪ ፡ ልምከርህ ፡ ደግሜ
ወደ ፡ ነፍስህ ፡ እረኛና ፡ ጠባቂ ፡ ና ፡ ተመለስ

ያለማወቅን ፡ ወራት ፡ ዘመናት ፡ እና ፡ ዓመታትም
ከኢየሱስ ፡ ወዲያ ፡ እርካታ ፡ ላይገኝ ፡ እንዲያው ፡ ስታልም
በዓለም ፡ የሚያንፅ ፡ ከቶ ፡ አይገኝም ፡ ምን ፡ ይሻልሃል
ድንቁ ፡ ኢየሱስን ፡ ተቀበለው ፡ ያረካሃል

አዝ፦ የባዘንከው ፡ ውድ ፡ ወንድሜ
አዳምጠኝ ፡ እስኪ ፡ ልምከርህ ፡ ደግሜ
ወደ ፡ ነፍስህ ፡ እረኛና ፡ ጠባቂ ፡ ና ፡ ተመለስ

ዕውቀትን ፡ አጥተህ ፡ በዚች ፡ ዓለም ፡ ላይ ፡ የተንከራተትክ
በጨለማው ፡ ገዥ ፡ በዲያቢሎስ ፡ እጅ ፡ የተማረክ
ምርኮን ፡ ለመካፈል ፡ ከላይ ፡ ከሰማይ ፡ የወረደው
የምስራቹን ፡ ትፈልታለህ ፡ አማኑኤል ፡ ነው

አዝ፦ የባዘንከው ፡ ውድ ፡ ወንድሜ
አዳምጠኝ ፡ እስኪ ፡ ልምከርህ ፡ ደግሜ
ወደ ፡ ነፍስህ ፡ እረኛና ፡ ጠባቂ ፡ ና ፡ ተመለስ (፪x)