መነቀፍን ፡ ፈርቶ (Meneqefen Ferto) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(3)

ክርስቲያን ፡ ተሻገረ
(Christian Teshagere)

ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)

ርዝመት (Len.): 3:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

በመንፈስ ፡ ጀምሮ ፡ ሮጦ ፡ ሮጦ
ከዓለም ፡ ማዕረግ ፡ መስቀል ፡ መርጦ
ዛሬ ፡ ግን ፡ በወሬ ፡ ልቡ ፡ ቀልጦ
መመካከር ፡ ያዘ ፡ ጠላት ፡ መርጦ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

እርግማን ፡ አይደለም ፡ መቃለሉ
መነቀፍ ፡ ክብር ፡ ነው ፡ አስተውሉ
ከአሁኑ ፡ ዓለም ፡ ተወዳጅቶ
ክርስቶስን ፡ መተው ፡ ይቅር ፡ ከቶ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

መስቀሉን ፡ ከጫንቃቸው ፡ ለጣሉ
እኛም ፡ ክርስቲያኖች ፡ ነን ፡ ለሚሉ
ይለፍ ፡ ለሌላቸው ፡ መንገደኞች
እንጸልይላቸው ፡ ለኮብላዮች

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ

መስጠሙን ፡ ቢረዳ ፡ ዓይኑ ፡ በርቶ
ንስሃ ፡ ቢገባ ፡ ዳግም ፡ ቀንቶ
እጅህ ፡ መቼ ፡ አጠረ ፡ የማዳንህ
ከጥልቁ ፡ ቢጣራ ፡ ድኩም ፡ ልጅህ

አዝ፦ መነቀፍን ፡ ፈርቶ ፡ ማመን ፡ አፍሮ
ውድ ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ፡ ቃልኪዳኑን ፡ ሰብሮ
ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ስንቱ ፡ ሰመጠ ፡ ባሕር ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ ቶሎ ፡ ድረስ ፡ እርዳኝ ፡ ብሎ ፡ እጁን ፡ ዘርግቶ ፡ ተጸጽቶ