From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የአደባባይ ፡ ሰው ፡ ሆነህ
በየማዕዘኑ ፡ ላይ ፡ ቆመህ
ሰውን ፡ አይተህ ፡ በሰው ፡ ታይተህ (፪x)
በስወር ፡ አይቶ ፡ በግልጥ ፡ የሚከፍልህን
በከፍታ ፡ ላይ ፡ የሚያስኬድህን
ረስተህ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ አሳዳጊ ፡ ጌታህን
በስውር ፡ የሚቀመጡ
ጌታቸውን ፡ የሚያደምጡ
የሕይወትን ፡ ቃል ፡ የሚያመጡ (፪x)
ሰውን ፡ ለማነጽ ፡ ነቅተው ፡ የሚታጠቁ
ለበጐ ፡ ሥራ ፡ ሁሉ ፡ የሚበቁ
ምስጉኖች ፡ ናቸው ፡ መማለድን ፡ የሚያዉቁ
ከእግዚአብሔር ፡ የተላከ
እርሱ ፡ ነው ፡ የተባረከ
ቃሉን ፡ ብቻ ፡ እየሰበከ (፪x)
አንተንስ ፡ ማነው ፡ አስነስቶ ፡ የላከህ
በፍጻሜው ፡ ላይ ፡ ትጠየቃለህ
እንደ ፡ ሥራህም ፡ ያኔ ፡ ትከፈላለህ
ሥራህ ፡ ድካምህ ፡ ብዙ ፡ ነው
አንተነትህን ፡ ያጐላው
ጌታ ፡ እንዳይታይ ፡ የጋረደው (፪x)
እስኪ ፡ በእውነት ፡ መርምረው ፡ ሕይወትህን
መፀለይ ፡ ትተህ ፡ መራቆትህን
ኢየሱስን ፡ ጋርደህ ፡ አንተ ፡ መታየትህን
ስማው ፡ ኢየሱስ ፡ ይመክርሃል
"ተው ፣ እረፍ ፣ ፀልይ" ፡ ይልሃል
ከእግሮቹ ፡ ሥር ፡ ሥጋህን ፡ ጣል (፪x)
ያን ፡ ጊዜ ፡ ጌታ ፡ በሰገነት ፡ ላይ ፡ ወጥቶ
ለዓለም ፡ ይታያል ፡ ብርሃኑ ፡ በርቶ
ሕይወት ፡ ይበዛል ፡ የስንዴው ፡ ቅንጣት ፡ ሞቶ
|