እንዲህ ፡ አልነበርኩም (Endih Alneberkum) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(2)

እግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ ነው
(Egziabhier Menfes New)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 4:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)

ሥምህን ፡ እንደዋዛ ፡ ተሽክሜዋለሁ
ክርስቲያን ፡ ተብዬም ፡ ይኸው ፡ እጠራለሁ
ውስጤ ፡ ቢመረመር ፡ ግን ፡ እንዲህ ፡ አይደለም
የመንፈስ ፡ ፍሬ ፡ ከቶ ፡ በእኔ ፡ የለም

አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)

የለየልኝም ፡ ከሃዲ ፡ አልሆንኩኝም
ክርስቲያንም ፡ ሆኜ ፡ አልበረታሁም
እንዲያው ፡ ለብ ፡ ብዬ ፡ አስቸግሬያለሁኝ
ዛሬስ ፡ በንስሃ ፡ ተደፍቻለሁኝ

አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)

ለክርስቲያኖች ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ፍቅር
ላገልግልህም ፡ ሥምህን ፡ ላስከብር
የነበረኝ ፡ ፀሎት ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ ትጋቴ
እፍገመገማለሁ ፡ ከድቶኛል ፡ ብርታቴ

አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)

ሽቅብ ፡ እንደመውጣት ፡ ቁልቁለት ፡ ሄጃለሁ
ወደ ፡ ሞትም ፡ ደጃፍ ፡ በጣም ፡ ቀርቤያለሁ
አሁንም ፡ በቃልህ ፡ ተገስጫለሁኝ
ዳግም ፡ አንሳኝ ፡ ብዬ ፡ ተማጽኛለሁኝ

አዝ፦ እንዲህ ፡ አልነበርኩም ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ ሆኛለሁ
ያን ፡ መልካሙን ፡ ሕይወት ፡ ከድሮ ፡ ውስጥ ፡ ፈልግያለሁ (፪x)