From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የጠላቴን ፡ እራስ ፡ ቀጥቅጠህ ፡ ከመጋጋው ፡ እኔን ፡ ነጥቀህ
ቅዱስ ፡ ደምህን ፡ አፍስሰህ ፡ ለሙት ፡ ልጅህ ፡ ሕይወት ፡ ሰጥተህ
ታላቁን ፡ መዳን፡ ድኛለሁ ፡ አሁንም ፡ መጽናት፡ አሻለሁ
አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ በስምህ: ጸንቼ : ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ ፡ እሩጫዬን ፡ ፈጽሜ
ስለዚህ ፡ ፈቃድህን ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ
ስቅበዘበዝ ፡ መክረኸኛል ፡ ስተክዝ ፡ አፅናንተኸኛል
ባቆስልህም ፡ ወደኸኛል ፡ ዘወትር ፡ ተሸክመኸኛል
እስከዛሬ ፡ ችለኸኛል ፡ ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ አቁሞኛል
አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ በስምህ፡ ፀንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ ፡ እሩጫዬን ፡ ፈጽሜ
ስለዚህ ፡ ፈቃድህን ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ
ዘወትር ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ ፡ አንተን ፡ ልምሰል ፡ አንተን ፡ ልፍራ
ከዓለም ፡ አድርገኝ ፡ ልዩ ፡ በእኔም ፡ ሕይወት ፡ አንተን ፡ ይዩ
ሥጋዬን ፡ ለዓለም ፡ ሰቅዬ ፡ ልጓዝ ፡ አንተን ፡ ተከትዬ
አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ በስምህ፡ ፀንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ ፡ እሩጫዬን ፡ ፈጽሜ
ስለዚህ ፡ ፈቃድህን ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ
በድካም ፡ ሕይወቴ ፡ ላልቶ ፡ አካሄዴም ፡ ተበላሽቶ
ቅዱስ ፡ ሥምህ ፡ አንዳይሰደብ ፡ አደራ ፡ ልጅህን ፡ አስብ
እስክትመጣልኝ ፡ በክብር ፡ አንተን ፡ አስከብሬ ፡ ልኑር
አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ በስምህ፡ ፀንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ ፡ እሩጫዬን ፡ ፈጽሜ
ስለዚህ ፡ ፈቃድህን ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ
በከፍታም ፡ በዝቅታም ፡ በሀዘንም ፡ በደስታም
ሳልደናገር ፡ በእርጋታ ፡ በፈተናም ፡ ሳልረታ
በትጋት ፡ ፀንቼ ፡ በእምነት ፡ ፊትህን ፡ ልየው ፡ በክበር
አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም ፡ በስምህ፡ ፀንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ ፡ እሩጫዬን ፡ ፈጽሜ
ስለዚህ ፡ ፈቃድህን ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ
|