From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ ልጅነቴ ፡ አላለቀም ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)
በግብዝነት ፡ ተሯሩጬም ፡ ከእውነትህም ፡ ተሳሰቼ
በስሜት ፡ ተገፋፍቼ ፡ የቃልህን ፡ ሙላት ፡ አጥቼ
እንዳልጠፋ ፡ በጠላት ፡ ተጠቅቼ
አዝ፦ ልጅነቴ ፡ አላለቀም ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)
ለጋነቴ ፡ እኔን ፡ አጋልጦኝ ፡ መከራውም ፡ አጠውልጐኝ
አውሎ ፡ ነፋስ ፡ አፍገምግሞኝ ፡ የአሸዋው ፡ መሠረት ፡ አዝሞኝ
ክፉኛ ፡ ገፍትሮ ፡ እንዳይጥለኝ
አዝ፦ ልጅነቴ ፡ አላለቀም ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)
ወተት ፡ ብቻ ፡ መጋቱን ፡ ትቼ ፡ አጥንቱንም ፡ ደግሞ ፡ በልቼ
እንደ ፡ ህጻን ፡ ማሰቤ ፡ ቀርቶ ፡ በጐልማሳነት ፡ ተተክቶ
ላይ ፡ እሻለሁ ፡ ሕይወቴ ፡ ተገንብቶ
አዝ፦ ልጅነቴ ፡ አላለቀም ፡ ነኝና ፡ ብላቴና
ሙሉ ፡ ሰው ፡ አድርገኝ ፡ ጌታ ፡ ቃልህን ፡ አብላኝና (፪x)
|