የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል (Yetefawen Man Yefelegal) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(7)

አልበም
(yayehal)

ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 4:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

ቤቱ ፡ ፈርሶ ፡ እያየህ ፡ የእግዚአብሔር
የራስህን ፡ ኑሮ ፡ ልታሳምር
ያለጌታ ፡ ልትከብር ፡ ሮጠሃል ፡ እስከዛሬ
ውስጡ ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ የጨበጥከው ፡ ፍሬ

አዝ፦ የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?

በጐቹ ፡ ለአራዊት ፡ መብል ፡ ሆኑ
እረኛ ፡ በማጣት ፡ ተበተኑ
ራስህን ፡ ስታሰማራ ፤ ለምቾትህ ፡ ስትሠራ
ይታይህ ፡ ወዳጄ ፡ የመንጋው ፡ መከራ

አዝ፦ የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?

መክሊትህ ፡ ወዴት ፡ ነው? ወንድሜ ፡ ሆይ!
እንደ ፡ ሃኬተኛው ፡ ቀበርከው ፡ ወይ?
የሰጠህ ፡ ይጠይቅሃል! አደራውን ፡ የት ፡ አድርገሃል?
የምትጠፋውን ፡ ነፍስ ፡ ከእጅህ ፡ ይፈልጋል

አዝ፦ የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?

ነፍስን ፡ ሊሰበስብ ፡ የተጠራ
ለጠፉት ፡ የሚያዝን ፡ የሚራራ
የምሥራች ፡ የሚያወራ
በፍጻሜው ፡ ይሸለማል
ዘለዓለም ፡ ይደምቃል ፡ እንደ ፡ ሰማይ ፡ ጸዳል

አዝ፦ የጠፋውን ፡ ማን ፡ ይፈልጋል?
የተጐዳውን ፡ ማን ፡ ያክማል?
ሰባራውን ፡ ማን ፡ ይጠግናል?
የፈረሰውን ፡ ማን ፡ ያድሳል?