እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን (Egna Gen Yemotelenen) - ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ
(Tesfaye Gabisso)

Lyrics.jpg


(4)

ምህረቱ ፡ አያልቅምና
(Meheretu Ayalqemena)

ቁጥር (Track):

፲ ፮ (16)

ርዝመት (Len.): 6:24
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ፡ አልበሞች
(Albums by Tesfaye Gabisso)

አይሁድ ፡ ምልክት ፡ ይለምናሉ
ግሪኮች ፡ ጥበብ ፡ ይሻሉ
ጌታን ፡ ስተው፡ ይቅበዘበዛሉ

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ያልገባቸው ፡ ቢያላግጡበትም
እንደ ፡ ሞኝነት ፡ ቢቆጥሩትም
በመስቀሉ ፡ ቃል ፡ አናፍርበትም

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

የመዳኑን ፡ ፀጋ ፡ መጠራቱን
ከኃጢአን ፡ መሃል ፡ መውጣቱን
ባይቀበሉትም ፡ እንኳን ፡ ወንጌሉን

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

እኛ ፡ ምልክታችን ፡ ኢየሱስ ፡
ጠበባችንም ፡ ክርስቶስ
አለቃችን ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ንጉሥ

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ባዶ ፡ ተስፋ ፡ ፍፁም ፡ አናወራም
ከሥጋችን ፡ አንዘራም
ጌታችን ፡ አለና ፡ አንፈራም

አዝ፦ እኛ ፡ ግን ፡ የሞተልንን
በደሙም ፡ የተቤዥንን
አዳኝነቱን ፡ ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እንሰብካለን
አዎን ፡ እንሰብካለን (፪x)

ለሚጠይቀን ፡ ሁሉ ፡ መልሳችን
የቀራንዮ ፡ ወዳጃችን
ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ስብከታችን