ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ (Getayawkal and Birucktawit)
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው በአለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)
ቤቴ ፡ አሸዋ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው እስከአሁን ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ ችግርም ፡ አላየሁ በጋው ፡ ተስማምቶኛል ፡ ምን ፡ ችግር ፡ ይመጣል ውኃ ፡ እኮ ፡ በአሸዋ ፡ ወዲያው ፡ ይመጠጣል
"መስሎሃል"
ይልቅ ፡ ወጪ ፡ አታውጡ ፡ አለት ፡ አትቧጥጡ ወጪን ፡ ይቀንሳል ፡ አሸዋ ፡ እኮ ፡ ሞልቷል የእኔስ ፡ ቤት ፡ አምራለች ፡ በጣም ፡ ዘንጣለች ላለሁበት ፡ ጊዜ ፡ ተመችታኛለች
"ተው ፡ ይቅርብህ"
አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
ክረምት ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ዝናብ ፡ የመጣ ፡ ቀን ጐርፉ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ንፋስ ፡ የመጣ ፡ ቀን ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር
ገንዘብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ዕውቀትህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት ሥልጣንህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ጥበብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
ችግር ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ሃዘን ፡ የመጣ ፡ ቀን መከራ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ማጣት ፡ የመጣ ፡ ቀን ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ባለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)
ቤቴ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ችግሩም ፡ በሽበሽ ፡ ነው ፡ መከራብ ፡ ብዙ ፡ ነው ጐርፉ ፡ ሲወርድብኝ ፡ ነፋስ ፡ ሲነፍስብኝ አለት ፡ ላይ ፡ ስላለሁ ፡ ቤቴ ፡ አልፈረሰብኝ
"ኧረ ፡ ምንም ፡ አትሆን"
አለት ፡ በቀላሉ ፡ አይገኝም ፡ ሲሉ የምደክም ፡ መስሎኝ ፡ ድሮ ፡ ተሞኘሁኝ የአሸዋ ፡ ነጋዴው ፡ ነበርና ፡ ወሬው ቤቴን ፡ በዓለት ፡ ብቻ ፡ ሰራሁ ፡ ከነአካቴው
"ደግ ፡ አድርገሃል"
አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት በቃ ፡ አለፈለት (፪x)
ክረምቱ ፡ ቢመጣ ፤ ዝናቡም ፡ ቢወርድ ጐርፉ ፡ ቢንደረደር ፤ ንፋሱም ፡ ቢነፍስ የአንተ ፡ ቤት ፡ እንደሆን ፡ ፈጽሞ ፡ አይላወስ
ኢየሱስ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ቃሉ ፡ ከሆነልህ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት በቃ ፡ አለፈለት (፪x)
መከራ ፡ ቢመጣ ፤ ችግር ፡ ቢደርስብህ ሃዘን ፡ ቢያጋጥምህ ፤ ማጣት ፡ ቢያስቸግርህ አትነቃነቅም ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ስላለህ
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
Contents
- 1 አልበሞች (Albums)
- 1.1 እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (Enkuan Des Alachehu) (Vol. Esp)
- 1.2 የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ (Ye11gnaw Seat Yetselot Teri) (Vol. 2006)
- 1.3 ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው (Barkotien Lequterew) (Vol. 2008)
- 1.4 ህጻናት ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጡ (Hetsanat Wede Enie Yemtu) (Vol. )
- 1.5 እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ይፈልጋል (Egziabhier Sewn Yefelegal) (Vol. )
- 1.6 ሽሽ ፡ ወጣቱ ፡ ሽሽ (Shesh Wetatu Shesh) (Vol. )
- 1.7 ምድር ፡ አለፈላት (Meder Alefelat) (Vol. 1)
- 2 የሕይወት ፡ ታሪክ (Biography)
አልበሞች (Albums)
እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ (Enkuan Des Alachehu) (Vol. Esp)
ልዩ ፡ እትም |
|
---|---|
ለመግዛት (Buy): |
የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ (Ye11gnaw Seat Yetselot Teri) (Vol. 2006)
፳ ፻ ፮ |
|
---|---|
ዓ.ም. (Year): | ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006) |
ለመግዛት (Buy): |
ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው (Barkotien Lequterew) (Vol. 2008)
፳ ፻ ፰ |
|
---|---|
ዓ.ም. (Year): | ፳ ፻ (2008) |
ለመግዛት (Buy): |
|
ህጻናት ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጡ (Hetsanat Wede Enie Yemtu) (Vol. )
|
|
---|---|
ለመግዛት (Buy): |
እግዚአብሔር ፡ ሰውን ፡ ይፈልጋል (Egziabhier Sewn Yefelegal) (Vol. )
|
|
---|---|
ለመግዛት (Buy): |
==={{{አልበም}}} (Lezelealem Amesegenehalehu
ካንተ የተነሳ በሆነልኘ ነገር
ከማመስገን በቀር እኔምን ልናገር
አስበሕ አቅደሕ በሰጠሕኘ በሙሉ
ጌታ ስምሕ ይክበር አመሰግናለሁ
ከኔ የሆነ የለም አንድም አለፏሁም
እንዲያው ሰተሕኟል ይሕን አረሳሁም ስለዚ ጌታዬ ለኔ ስላረከው
ተረድቻለሁ ስምሕን ላክበረው
አድርገሕልኛል ካይምሮዬ በላይ
ጌታዬ ተባረክ ሰምድርም በሰማይም/×3
አድርገሕልኝልና ለዘላለም አመሰግንሀለው
እድሜዬን በሙሉ ብለፍና ብጥር
የማላገኘውን ሰማያዊ ሚስጥር
ለልቤ ተናግረሕ ልቤንም ማረከው
ከዚሕ ሁሉ በላይ የራስሕ አረከዉ
እኔም ተስማምቼ በፍቅርሕ ተማረኲኘ
አምላኬ ጌታዬ ምርጫዬ አደረኩኘ
አንተ ከመረጥከኘ ወዴት እሄዳለሁኘ
ካንተ የበለጠ ምንስ አገኛለሁ
ይሕንን ላረከው በልብሕ ላሰብከኘ
ላንተ ለአምላኬ ሁሌ እገዛለሁኘ/×3
አድርገሕልኝልና ለዘላለም አመሰግንሀለው posted by natan mersha😊🙌✌) (Vol. 2005)===
፳ ፻ ፭ |
አልበም ካንተ የተነሳ በሆነልኘ ነገር ከማመስገን በቀር እኔምን ልናገር አስበሕ አቅደሕ በሰጠሕኘ በሙሉ ጌታ ስምሕ ይክበር አመሰግናለሁ ከኔ የሆነ የለም አንድም አለፏሁም እንዲያው ሰተሕኟል ይሕን አረሳሁም ስለዚ ጌታዬ ለኔ ስላረከው ተረድቻለሁ ስምሕን ላክበረው አድርገሕልኛል ካይምሮዬ በላይ ጌታዬ ተባረክ ሰምድርም በሰማይም/×3 አድርገሕልኝልና ለዘላለም አመሰግንሀለው እድሜዬን በሙሉ ብለፍና ብጥር የማላገኘውን ሰማያዊ ሚስጥር ለልቤ ተናግረሕ ልቤንም ማረከው ከዚሕ ሁሉ በላይ የራስሕ አረከዉ እኔም ተስማምቼ በፍቅርሕ ተማረኲኘ አምላኬ ጌታዬ ምርጫዬ አደረኩኘ አንተ ከመረጥከኘ ወዴት እሄዳለሁኘ ካንተ የበለጠ ምንስ አገኛለሁ ይሕንን ላረከው በልብሕ ላሰብከኘ ላንተ ለአምላኬ ሁሌ እገዛለሁኘ/×3 አድርገሕልኝልና ለዘላለም አመሰግንሀለው posted by natan mersha😊🙌✌) |
---|---|
ዓ.ም. (Year): | ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005) |
ለመግዛት (Buy): |
|
ሽሽ ፡ ወጣቱ ፡ ሽሽ (Shesh Wetatu Shesh) (Vol. )
|
|
---|---|
ለመግዛት (Buy): |
|
ምድር ፡ አለፈላት (Meder Alefelat) (Vol. 1)
፩ |
|
---|---|
ዓ.ም. (Year): | ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002) |
ለመግዛት (Buy): |
|
የሕይወት ፡ ታሪክ (Biography)
ስለ | |
ዘማሪ: | ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ |
ፆታ: | ወንድና ፡ ሴት |
ትውልድ: | ኢትዮጵያ |
የአልበም ፡ ብዛት: |
፮ (6) |
Last Update: | April 20, 2014 |
GetaYawkal and Biruktawit have been serving the Lord for more than 26 years in Ethiopia and abroad. These duet singers started their ministry from Sunday school. So far they have produced six different song albums and participated producing Collection Albums with other singers. Their special music albums include songs for Little Children and for Youth Group, Wedding Songs and songs specially dedicated for Prayer Time.