ጌታ ፡ ለሕይወቴ (Gieta Lehiwotie) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ሽሽ ፡ ወጣቱ ፡ ሽሽ
(Shesh Wetatu Shesh)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 4:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

ጌታ ፡ ለሕይወቴ ፡ አንተ ፡ መሪ ፡ ሁነህ
ለኑሮዬም ፡ ጥላ ፡ ሃሩር ፡ እንዳይጐዳኝ
እባክህ ፡ ሁንልኝ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ
አንተ ፡ ግን ፡ ብርቱ ፡ ነህ ፡ ጸንተህ ፡ የምትገኝ

ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለልጅህ ፡ የምታውቅ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሚበጀኝንም ፡ ሁሉን ፡ አዘጋጅተህ
ለእኔ ፡ ታስባለህ ፡ ትጠነቀቃለህ
የማይጠቅመኝንም ፡ ወዲያ ፡ ትጥላለህ

የልቤ ፡ ጓደኛ ፡ በአንተ ፡ እረካለሁ
የምትሰጠኝንም ፡ እቀበልሃለሁ
ሁሉን ፡ እንደወደድህ ፡ እንደ ፡ ፈቃድህ
እንግዲህ ፡ አድርገው ፡ ደስ ፡ እንዳሰኘህ

ከእንግዲህስ ፡ እኔ ፡ ምንም ፡ አልናገር
ሰጥቼዋለሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ለእግዚአብሔር
በደስታም ፡ በሃዘን ፡ ተመስገን ፡ እያልሁኝ
እርሱም ፡ ሚያደርገውን ፡ እኔ ፡ አያለሁኝ

አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን