ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ (Serahen Tefetsemaleh) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 1.jpg


(1)

ምድር ፡ አለፈላት
(Meder Alefelat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:13
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል
ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ፡ ማነው
ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)

ባለፈው ፡ ዘመን ፡ የሰራ ፡ ዛሬም ፡ ክንዱ ፡ ያልደከመ
መንግሥቱን ፡ በደንብ ፡ አስፋፋ ፡ እኛም ፡ ደግሞ ፡ የቀጠለ
ኃይል ፡ ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ሆኖልን ፡ የምንሰራው ፡ አብረን ፡ ነው
አሁን ፡ ካሳየን ፡ ይበልጣል ፡ ነገን ፡ በእኛ ፡ የሚገልጠው

ሰራተኛ ፡ አድርጐናል ፡ ለቤቱ
መስራት ፡ ያላቆመ ፡ ከጥንቱ
በሚሰራበት ፡ ቀን ፡ በቤቱ
መጠቀሚያው ፡ ነን ፡ እኛ ፡ ገንዘቡ (፪x)

አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል
ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ፡ ማነው
ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)

በአሁኑ ፡ ዓመት ፡ እንዳየነው ፡ በሚመጣው ፡ ዓመት ፡ አይሆንም
ብሶበት ፡ እንጂ ፡ ቀንሶ ፡ ሥራው ፡ አይከናወንም
እጥፍ ፡ ድርብ ፡ እየሆነ ፡ ፍሬው ፡ ገና ፡ ይበዛልናል
በክልል ፡ አይወሰንም ፡ የምድርን ፡ ፊት ፡ ይሸፍናል

የምሩን ፡ ይነሳል ፡ ንጉሡ
እናንተ ፡ አገልጋዮች ፡ ተነሱ
ገና ፡ ብዙ ፡ ጉድ ፡ ነው ፡ የሚታየው
እግዚአብሔር ፡ ሀሳቡ ፡ እኛ ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል
ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ፡ ማነው
ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)

ዛሬ ፡ ከተገለጠልን ፡ የነገው ፡ ደግሞ ፡ ይብሳል
የሚመጣልን ፡ ዝማሬ ፡ የዛሬን ፡ ሁሉ ፡ ያስረሳል
ማሽቆልቆል ፡ ወደታች ፡ መውረድ ፡ መቀነስ ፡ መዳከም ፡ መዛል
ከዚህ ፡ በኋላ ፡ በእኛ ፡ ላይ ፡ በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አይሰራም

ተሻገር ፡ የሚል ፡ ወደ ፡ ማዶ
ሰምተናል ፡ ድምፅ ፡ ከሰማይ ፡ ወርዶ
ተሻግረን ፡ ደግሞ ፡ እንሄዳለን
የነገውን ፡ ዘመን ፡ እናያለን (፪x)

አዝ፦ በዘመን ፡ በዓመታት ፡ መሃል
ሥራህን ፡ ትፈፅማለህ
የሚከለክልህ ፡ ማነው
ኢየሱስ ፡ ኃይልህ ፡ ብርቱ ፡ ነው (፪x)