From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)
የችግር ፡ ቋጠሮ ፡ ውስብስብ ፡ ሲልብኝ
መግቢያ ፡ መውጫ ፡ ጠፍቶህ ፡ ግራ ፡ ሲያጋባኝ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ደግሞ ፡ ሲፈታታ ፡ ችግር ፡ ሁሉ ፡ ሲተን
የትላንት ፡ ጨለማ ፡ እንደጉም ፡ ሲበተን
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)
አንተን ፡ እንዳላመልክ ፡ ከፍታው ፡ ዝቅታ
ከቶ ፡ አያግደኝም ፡ አይጠፋኝ ፡ ዕልልታ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ውስጤ ፡ ቅኔ ፡ ሞልቷል ፡ ከገጠመኝ ፡ በላይ
አምላኬ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህና ፡ ኤልሻዳይ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ጠፍቶ ፡ በቤቴ ፡ የሚበላ
ያልጠበኩት ፡ ነገር ፡ ሲሆንብኝ ፡ ሌላ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
ደግሞ ፡ በጐጆዬ ፡ በረከት ፡ ሲሞላ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ሞልቶ ፡ ሲተርፈኝ ፡ ለሌላ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)
ሲሞላ ፡ ዘምሬ ፡ ሲጐድል ፡ ላላለቅስ
በምንም ፡ ሁኔታ ፡ አምልኮ ፡ አልቀንስም
አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ
እታመንሃለሁ ፡ በምሥጋና ፡ ሆኜ
ድል ፡ እንደምትሰጠኝ ፡ በስምህ ፡ አምኜ
አንተ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ ፡ ነህ
አዝ፦ አተገመትም ፡ በእኔ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በአእምሮ ፡ ስፋት
አትገመትም ፡ በሺህ ፡ ቃላት ፡ ብዛት
አትወሰንም ፡ በጠቢባን ፡ ጥበብ
አንተ ፡ ከሁሉ ፡ በላይ ፡ ነህ ፤ በላይ ፡ ነህ (፪x)
|