ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር (Mesgana LeEgziabhier) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 4:02
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

 
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ፤ ምሥጋና
ሁለቱን ፡ ሙሽሮች ፡ አንድ ፡ አድርጓልና ፤ ምሥጋና (፪x)

የደስታ ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ
የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ የዝማሬ
እግዚአብሔር ፡ ስለረዳቸው
ኑሮም ፡ መሰረተላቸው
የፍቅርን ፡ ቤት ፡ ሰራላቸው

ባሳለፉት ፡ ዘመናቸው
መከራ ፡ እንኳን ፡ ቢገጥማቸው
በዚያ ፡ ሁሉ ፡ አግዟቸው
ከክፉ ፡ ሃሳብ ፡ ጠብቋቸው
ዛሬ ፡ ለዚህ ፡ አበቃቸው

አዝ፦ ምሥጋና ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ፤ ምሥጋና
ሁለቱን ፡ ሙሽሮች ፡ አንድ ፡ አድርጓልና ፤ ምሥጋና (፪x)

በሶስትም ፡ የተገመደ ፡ አይበጠስ ፡ አይበጠስ
ጌታ ፡ እስካለ ፡ ድረስ (፬x)

ተከናወነ ፡ ብቸኝነት ፡ ቀረ
ጌታ ፡ ያስደስታል ፡ እያጣመረ ፡ እያስተሳሰረ (፪x)

አሃሃ ፡ ፊታቸው ፡ አሃሃ ፡ አላፈረም
አሃሃ ፡ ጋብቻው ፡ አሃሃ ፡ ስመረ (፰x)