እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን (Esti Lelemenew Gietayien) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 2006.jpeg

፳ ፻ ፮
(2006)

የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
(Ye11gnaw Seat Yetselot Teri)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

 
ስለዚህ ፡ ወደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ልመና
ጸሎት ፡ ምልጃና ፡ ምሥጋና
ለሰዎች ፡ ሁሉ ፡ እንዲደረግ ፡ ከሁሉም ፡ በፊት ፡ እመክራለሁ
በመንፈሳዊነትና ፡ በመልካም ፡ ጠባይ ፡ እየተመራን
በሰላምና ፡ በጸጥታ ፡ እንድንኖር ፡ በተለይ
ለነገሥታትና ፡ በስልጣን ፡ ላይ ፡ ላሉ ፡ ሁሉ ፡ ጸልዩ

አዝ፦ እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለህዝቤ
የራሴን ፡ የግሌን ፡ ነገር ፡ ትቼ
እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለምድሬ
የራሴን ፡ የጸሎት ፡ ርዕስ ፡ ትቼ
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች (፪x)

የአገሬ ፡ መፍትሄዋ ፡ የእንቆቅልሿ ፡ መፍቻዋ
ቁልፉ ፡ ያለው ፡ ሰው ፡ ጋር ፡ አይደል
ታዲያ ፡ ማንም ፡ አይታለል
ስለእልቂቷ ፡ ወሬን ፡ ትቼ ፡ ስንበረከክ ፡ ተደፍቼ
ይሰማኛል ፡ አምነዋለሁ ፡ ከዚም ፡ በፊት ፡ አይቻለሁ
ሁሉም ፡ ነገር ፡ ያበጀዋል ፡ ዝብርቅርቁን ፡ ያሳምራል

አዝ፦ እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለህዝቤ
የራሴን ፡ የግሌን ፡ ነገር ፡ ትቼ
እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለምድሬ
የራሴን ፡ የጸሎት ፡ ርዕስ ፡ ትቼ
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች (፪x)

በችግሯ ፡ ከምሳለቅ ፡ ይልቅ ፡ እኔ ፡ ፊቱ ፡ ልውደቅ
ባለምነው ፡ ባልጠይቀው ፡ እዳው ፡ በእኔ ፡ ጫና ፡ ላይ ፡ ነው
መፍትሄ ፡ ላይሆን ፡ ወሬን ፡ ትቼ ፡ ልንበረከክ ፡ ፊቱን ፡ ሽቼ
ሰሚ ፡ አምላክ ፡ እያመንኩኝ ፡ ለምን ፡ መፍትሄ ፡ አጣለሁኝ
ትልቅም ፡ ለውጥ ፡ አመጣለሁ ፡ ለምድሬም ፡ ፈውስ ፡ እሆናለሁ

አዝ፦ እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለህዝቤ
የራሴን ፡ የግሌን ፡ ነገር ፡ ትቼ
እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለምድሬ
የራሴን ፡ የጸሎት ፡ ርዕስ ፡ ትቼ
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች (፪x)

ብለምነው ፡ ስለአገሬ ፡ ሸክም ፡ ቢኖረኝ ፡ ለምድሬ
ያለባትን ፡ ችግር ፡ ሁሉ ፡ ይዤ ፡ ብቀርብ ፡ ከመስቀሉ
ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ያደምጠኛል ፡ እንደሃሳቡ ፡ ይመልሳል
ሳልታክት ፡ ፊቱ ፡ እቀርባለሁ ፡ ቃሉም ፡ ይላል ፡ ጸልያለሁ
ሸክሟን ፡ ሳሳየው ፡ የምድሬን ፡ ይፈውሳታል ፡ አገሬን

አዝ፦ እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለህዝቤ
የራሴን ፡ የግሌን ፡ ነገር ፡ ትቼ
እስቲ ፡ ልለምነው ፡ ጌታዬን ፡ ስለአገሬ ፡ ስለምድሬ
የራሴን ፡ የጸሎት ፡ ርዕስ ፡ ትቼ
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች
ለሹማምንት ፡ ለገዢዎች ፡ ለአለቆች
ፊቱ ፡ ልቅረብ ፡ ልጸልይ ፡ ተግቼ ፡ ስለሌሎች (፪x)

ኢትዮጵያን ፡ ግብኛት ፡ ተመልከታት
በቃልኪዳንህ ፡ አስባት (፬x)