መስቀልህ ፡ ስር (Mesqeleh Ser) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 2006.jpeg

፳ ፻ ፮
(2006)

የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
(Ye11gnaw Seat Yetselot Teri)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

 
ተስፋ ፡ ቆርጬ ፡ ወደኋላዬ ፡ አልልም
በጥቂቱ ፡ ዝዬ ፡ አልመለስም
ብትገድለኝም ፡ ብታድነኝም
ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም
እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም

አንተን ፡ የለመነህ ፡ በፊትህ ፡ ጠብቆ
ሁሉን ፡ እንደምትችል ፡ እንደምትሰጥ ፡ አውቆ
ጊዜውን ፡ ብታረዝምም ፡ እምነቱን ፡ ልትፈትን
እርሱን ፡ የጠበቀው ፡ መች ፡ አጣው ፡ ባርኮቱን
አግኝቷል ፡ ከጌታ ፡ አጽንቶ ፡ እምነቱን

እኔም ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ እጠብቃለሁ
ምን ፡ እንደምትሰራ ፡ እጅህን ፡ አያለሁ
ጉልበቴን ፡ በፊትህ ፡ አምበረክካለሁ
ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ
አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ

አንዲት ፡ ከነአናዊት ፡ ሴት ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ መጥታ
'የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ልጄ ፡ በእርኩስ ፡ መንፈስ
ተይዛ ፡ ትስቃያለችና ፡ እባክህ ፡ እራራልኝ' ፡ እያለች ፡ ጮኸች
እርሱ ፡ ግን ፡ አንድም ፡ ቃል ፡ ሳይመልስላት ፡ ዝም ፡ አለ
በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ደቀ ፡ መዛሙርቱ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ቀረብ ፡ ብለው
'ይሂች ፡ ሴት ፡ እየተከተለችን ፡ ስለምትጮህ ፡ እባክህ ፡ አሰናብታት' ፡ ሲሉ ፡ ለመኑት
እርሱም ፡ 'እኔ ፡ የተላኩት ፡ ከእስራኤል ፡ ቤት ፡ እንደበጐች ፡ ለጠፉት ፡ ብቻ ፡ ነው'
ሲል ፡ መለሰ። ሴትዬዋ ፡ ግን ፡ ቀርባ ፡ በእግሩ ፡ ስር ፡ ተንበረከከችና
'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ አለችው'።
ኢየሱስም ፡ 'የልጆችን ፡ እንጀራ ፡ ወስዶ ፡ ለውሾች ፡ መጣል ፡ የተገባ ፡ አይደለም' ፡ አለ።
እርሷም ፡ 'ጌታ ፡ ሆይ ፡ እርግጥ ፡ ነው። ነገር ፡ ግን ፡ ውሾችም ፡ እኮ
ከጌቶቻቸው ፡ ማዐድ ፡ የወደቀውን ፡ ፍርፋሪ ፡ ይበላሉ' ፡ አለችው።
በዚያን ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ 'አንቺ ፡ ሴት ፡ እምነትች ፡ ትልቅ ፡ ነው።
ስለዚህ ፡ እንደፍላጐትሽ ፡ ይሁንልሽ ፡ አላት'።
የሴትየዋም ፡ ልጅ ፡ በዚያን ፡ ሰዓት ፡ ዳነች።

በለእርሱን ፡ የጠበቀ ፡ ፍሬዋን ፡ ይበላል
ከጌታው ፡ ሚጠብቅ ፡ እርሱ ፡ ደግሞ ፡ ይከብራል
እኔም ፡ ከአንተ ፡ ብቻ ፡ እጠብቃለሁኝ
የአማረውን ፡ ፍሬ ፡ ለመብላት ፡ ጓጓሁኝ
አይቀርም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ደግሞ ፡ እከብራለሁኝ

ብትሰጠኝም ፡ ብትነሳኝም
እጅህን ፡ እጠብቃለሁ ፡ ከፊትህ ፡ አልሄድም
ቃሌንም ፡ በቤትህ ፡ ዝም ፡ አሰኘዋለሁ
አንተ ፡ ምትሰራውን ፡ በሙሉ ፡ አያለሁ