From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አቤቱ ፡ በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን
በመድሃኒትህም ፡ ጐብኘን
ህዝብህ ፡ ለአርባ ፡ አመታት ፡ ሲጓዝ ፡ ምድረ ፡ በዳ
ሞገስ ፡ ስለሆንከው ፡ ከቶ ፡ ሳይጐዳ
እያዘነብክለት ፡ ከሰማያት ፡ መና
ስትጠብቅ ፡ ስትመራው ፡ በእሳት ፡ በደመና
ሞገስህን ፡ አግኝቶ ፡ ህዝብህም ፡ በርትቶ
ድል ፡ በድል ፡ አድርጓል ፡ ጠላቶቹን ፡ ረግጦ
ህዝብህን ፡ ባሰብክበት ፡ ሞገስህ ፡ አስበን
ማምለጥ ፡ እንድንችን ፡ ከከበበን ፡ ነገር
አዝ፦ በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
ያየ ፡ የጋለው ፡ ፍቅርህ ፡ የቀድሞው ፡ ሕይወታችን
ዛሬ ፡ ቀስሞብናል ፡ ቀዝቅዟል ፡ ልባችን
አንድነት ፡ ሲጠፋ ፡ መለያየት ፡ በዝቶ
ስም ፡ ብቻ ፡ ሆነናል ፡ ሕይወታችን ፡ ሞቶ
ዛሬ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ጐብኘን ፡ በ???
ባሰብክበት ፡ ምህረት ፡ ልክ ፡ እንደህዝቦችህ
እጆቿን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ኢትዮጵያም ፡ ትዘርጋ
ጊዜው ፡ አሁን ፡ ይሁን ፡ ሞገስህ ፡ ይብዛና
አዝ፦ በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
በአንደበት ፡ ፍቅር ፡ የለበጥ ፡ አንድነት
ቤትህን ፡ አረግነው ፡ ተንኮል ፡ የሞላበት
በአፋችን ፡ ሌላ ፡ በልባችን ፡ ሌላ
የያዝነውን ፡ እምነት ፡ አረግነው ፡ ደካማ
መግባባት ፡ ይኑረን ፡ ቃላችን ፡ አንድ ፡ ይሁን
እንደተናገርነው ፡ እንዲሁ ፡ እንድንኖር
ዛሬ ፡ ለውጥን ፡ ስጠን ፡ ጌታ ፡ ለሁላችን
በሞገስህ ፡ አስበን ፡ ይቀየር ፡ ልባችን
አዝ፦ በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
በህዝብህ ፡ ሞገስ ፡ አስበን (፬x)
|