እግዚአብሔርን ፡ መምሰል (Egziabhieren Memsel) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 1.jpg


(1)

ምድር ፡ አለፈላት
(Meder Alefelat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(7)

ርዝመት (Len.): 5:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

ለሥጋዊ ፡ ነገር ፡ እራስን ፡ ማስለመድ
ከእግዚአብሔር ፡ ሀሳብ ፡ እርቆ ፡ መራመድ
ለጊዜያዊ ፡ ደስታ ፡ ነፍስን ፡ አስገዝቶ
ዛሬን ፡ ብቻ ፡ መኖር ፡ የነገውን ፡ ትቶ

አይጠቅመኝም ፡ ከቶ ፡ ይህን ፡ አውቄዋለሁ
እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ
ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው

በሰው ፡ ወግ ፡ ተይዞ ፡ በይሉኝታ ፡ እስራት
ዛሬን ፡ ላያሻግር ፡ ለእንጀራ ፡ መገዛት
እውነትን ፡ ከመግለጥ ፡ በውሸት ፡ ከልሎ
መምሰል ፡ የሌለበት ፡ የማስመሰል ፡ ኑሮ

አይጠቅመኝም ፡ ከቶ ፡ ይህን ፡ አውቄዋለሁ
እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ
ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው

ታላቅና ፡ ክቡር ፡ ሕይወትም ፡ የሆነ
ከአማራጮች ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ የተሻለ
አሁን ፡ ላለውና ፡ ለመጪው ፡ ዘመኔ
እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ያዋጣኛል ፡ ለእኔ

ያዋጣኛል ፡ አዎ ፡ ይህን ፡ አውቄያለሁ
እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው
ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሪያለሁ
ጥማቴም ፡ ናፍቆቴም ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው

ከኋላ ፡ ያለውን ፡ በሙሉ ፡ ረስቼ
የፊቴን ፡ ለመያዝ ፡ እጆቼን ፡ ዘርግቼ
ምልክት ፡ አይቼ ፡ መፍጠን ፡ ጀምሬያለሁ
መጠራቴ ፡ ዋጋው ፡ ጌታዬን ፡ መምሰል ፡ ነው

ብዬ ፡ ተናግሬ ፡ ጉዞ ፡ ጀምሬያለሁ
እግዚአብሔርን ፡ መምሰል ፡ ለእኔ ፡ ማትረፊያ ፡ ነው
ስለዚህ ፡ የሚይዘኝ ፡ የሚያስቀረኝ ፡ ማነው
ሁሉንም ፡ እየጣስኩ ፡ ወደፊት ፡ ሄዳለሁ