እሩህሩህ ፡ ነህ (Eruhruh Neh) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 1.jpg


(1)

ምድር ፡ አለፈላት
(Meder Alefelat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 7:53
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

ዓይኖችህ ፡ አይጨክኑም ፡ ፊትህን ፡ አታዞር
ዘወትር ፡ እሩህሩህ ፡ ነህ ፡ ተመስገን ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ዓይኔ ፡ ማዳንህን ፡ አይቷል ፡ ምህረትህን
ልቤም ፡ ይሄ ፡ ገብቶት ፡ ያከብራል ፡ ስምህን (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

የኃጢአቴ ፡ ድንቀት ፡ እንዳለላ ፡ እንደደም ፡ ብትቀላ
ኃጢአቴን ፡ እንጂ ፡ እኔን ፡ መቼም ፡ ቢሆን ፡ ከቶ ፡ አጥጠላ
ታዲያ ፡ በምህረትህ ፡ በከበረው ፡ ደምህ ፡ ታጥበኝና
ልጅ ፡ ታደርገኛለህ ፡ በይቅርታ ፡ ጠርተህ ፡ እንደገና
ክስ ፡ ቢበዛብኝ ፡ በአይምሮዬ ፡ ቢቆሽሽብኝ ፡ ህሊናዬ
ነገር ፡ ግን ፡ ደምህን ፡ ተማምኜ ፡ ምህረትህ ፡ ነው ፡ ቤቴ (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ዓይኖችህ ፡ አይጨክኑም ፡ ፊትህን ፡ አታዞር
ዘወትር ፡ እሩህሩህ ፡ ነህ ፡ ተመስገን ፡ እግዚአብሔር
ዓይኔ ፡ ማዳንህን ፡ አይቷል ፡ ምህረትህን
ልቤም ፡ ይሄ ፡ ገብቶት ፡ ያከብራል ፡ ስምህን (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ

ምህረትህ ፡ ርህራሄህ ፡ አላለቀም ፡ እስከዛሬ ፡ ድረስ
ፍጥረት ፡ ውሎ ፡ የገባው ፡ ስለዚህ ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ በመታገዝ
ለእኔም ፡ ይሄ ፡ እድል ፡ ቢደርሰኝም ፡ ግን ፡ ተጨመረልኝ
በልጅህ ፡ አምኜ ፡ በዳንኩኝ ፡ ለት ፡ ምህረትህ ፡ በዛልኝ

ሳስበው ፡ ለእኔ ፡ ያለህን ፡ ፍቅር
ቀላል ፡ አይደለም ፡ የሚነገር
እርሱን ፡ ተማምኜ ፡ እኖራለሁ
አገለግላለሁ (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)

ዓይኖችህ ፡ አይጨክኑም ፡ ፊትህን ፡ አታዞር
ዘወትር ፡ እሩህሩህ ፡ ነህ ፡ ተመስገን ፡ እግዚአብሔር (፪x)

ዓይኔ ፡ ማዳንህን ፡ አይቷል ፡ ምህረትህን
ልቤም ፡ ይሄ ፡ ገብቶት ፡ ያከብራል ፡ ስምህን (፪x)

ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ሃሌሉያ ፡ ሃሌሉያ ፡ አሜን (፬x)
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ
ኦ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ