ሰላም ፡ አለ ፡ ለእኔ (Selam Ale Lenie) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 2008.jpg

፳ ፻ ፰
(2008)

ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው
(Barkotien Lequterew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 10:00
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝሰላም ፡ አለኝ (፫x) ፡ በልቤ ፡ በልቤ
ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ አንብቤ ፡ ደህንነት ፡ አግኝቻለሁ
በጌታ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ

ሰላሜ ፡ በውስጤ ፡ እንዲህ ፡ የፈሰሰው
ኢየሱስ ፡ በደሙ ፡ ሕይወቴን ፡ ገዝቶት ፡ ነው
በጭንቅ ፡ ከመወጠር ፡ አዕምሮዬ ፡ ያረፈው
እረፍት ፡ የሚሰጠው ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ፡ ነው

ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ
ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ
በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ
በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ
እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x)

አዝሰላም ፡ አለኝ (፫x) ፡ በልቤ ፡ በልቤ
ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ አንብቤ ፡ ደህንነት ፡ አግኝቻለሁ
በጌታ ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ

ልቤ ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ እንዲህ ፡ ያፈለቀው
የእግዚአብሔር ፡ ሃሳብ ፡ ሕይወቴን ፡ ሞልቶት ፡ ነው
ልቤን ፡ ለእርሱ ፡ አርፎ ፡ ተዋርዶ ፡ የተገዛው
እውነተኛ ፡ ፍቅሩን ፡ አውቆ ፡ ተረድቶት ፡ ነው

ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ሰላሜ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ

ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ
ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ
በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ
በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ
እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x)

በጤንነት ፡ ሆኜ ፡ መውጣቴ ፡ መግባቴ
ኢየሱስ ፡ ሆኖልኝ ፡ ነው ፡ ኃይልና ፡ ጉልበቴ
ወደ ፡ መልካም ፡ ስፍራ ፡ እግሬ ፡ የሚሮጠው
እግሬን ፡ የሚመራ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖ ፡ ነው

ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ፈዋሼ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ

ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ
ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ
በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ
በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ
እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x)

አቅሜ ፡ የእርሱን ፡ ስራ ፡ እንዴት ፡ ሊናገረው
የእርሱ ፡ ውለታ ፡ በልቤ ፡ ሞልቶ ፡ ነው
ልቤም ፡ መስቀሉ ፡ ስር ፡ ስለተዋረደ
የእግዚአብሔር ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ ነደደ

ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ
ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ
በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ
በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ
እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x)

አዝተለወጥኩኝ (፫x) ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ
አዲስ ፡ ፍጥረት ፡ ሆኛለሁ
መንፈሱን ፡ አግኝቻለሁ
በጌታ ፡ ለውጥን ፡ አግኝቻለሁ

የእግዚአብሔር ፡ ማዳን ፡ ለሰው ፡ የማወራው
ማዳኑን ፡ በዐይኔ ፡ ስለአየሁኝ ፡ ነው
ሰዎችን ፡ ለመውደድ ፡ ለማፍቀር ፡ የቻልኩት
በጌታዬ ፡ ፍቅር ፡ ስላገኘውሁ ፡ ነው ፡ እረፍት

እረፍት ፡ አለኝ (፫x) ፡ በኢየሱስ ፡ በኢየሱስ
የማይጠፋ ፡ ደስታ ፡ የማይለወጥ ፡ ተስፋ
በሕይወቴ ፡ በጣም ፡ ተስፋፋ

ባይሆንማ ፡ ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ባይኖርልኝ
ሕይወቴን ፡ ባይገዛው ፡ ባይቆጣጠረኝ
በጭንቀት ፡ ተይቬ ፡ ጉስቁልና ፡ ከቦኝ
በስቃይ ፡ ተውጬ ፡ ነበረ ፡ የምገኝ
ግን ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ ፡ እርሱ ፡ ስላለልኝ
እረፍት ፡ አግኝቻለሁ ፡ ተፈትቻለሁኝ (፪x)

ሕይወቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ ፈዋሼ ፡ ነው ፡ ነው
እረፍቴ ፡ ነው ፡ ነው ፡ አቅሜ ፡ ነው
የምመካበት ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ
ለእኔስ ፡ ኢየሱሴ ፡ ካለ