ምድር ፡ አለፈላት (Meder Alefelat) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 1.jpg


(1)

ምድር ፡ አለፈላት
(Meder Alefelat)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፭ (2002)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 10:36
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

እግዚአብሔርም ፡ በሠራዊቱ ፡ ፊት ፡ ድምጹን ፡ ይሰጣል
ሰራዊቱም ፡ ይህን ፡ ይመስላል
መልካቸው ፡ እንደ ፡ ፈረስ ፡ መልክ ፡ ነው
የማንኮራፋቱ ፡ ክብር ፡ የሚያስፈራ ፡ ነው
በኮቴው ፡ በሸለቆው ፡ ውስጥ ፡ ይጐደፍራል
በፍርሃት ፡ ላይ ፡ ይስቃል ፣ አይደነግጥም
ከሰይፍ ፡ ፊቱን ፡ አይመልስም
የመለከትን ፡ ድምጽ ፡ ሲሰማ ፡ እሰይ ፡ ይላል
ገለባውንም ፡ እንደሚባላ ፡ እንደ ፡ እሳት ፡ ድምጽ
ለሰልፍም ፡ እንደተዘጋጀ ፡ ለብርቱ ፡ ሕዝብ ፡ ያኮበኩባል
እንደ ፡ ኃያላን ፡ ይሮጣሉ ፡ ከሰልፈኞችም ፡ በቅጥር ፡ ይወጣሉ
እንደ ፡ ሌባም ፡ በመስኮት ፡ ይገባሉ
እያንዳንዱ ፡ በመንገዱ ፡ ይራመዳል
የራሱን ፡ መንገድ ፡ ይጠበጥባል ። ከእነርሱ ፡ የሚያመልጥ ፡ የለም ።
ምድሪቱም ፡ ከፊታቸው ፡ የተነሳ ፡ ትናወጣለች ።
እነሆ ፡ እንዲህ ፡ ያለ ፡ ሠራዊት ፡ በምድረ ፡ ኢትዮጵያ ፡ ይገለጣል
አሜን! ፡ ሃሌሉያ!

አዝምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
መልኩ ፡ የፈረስ ፡ ሩጫው ፡ የፈረስ
አንዴ ፡ ከገባ ፡ የማይመለስ
ዓይኑ ፡ የፈረስ ፡ ድፍረት ፡ የፈረስ
አንዴ ፡ ከመጣ ፡ የማይመለስ

አዝምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
አንገቱ ፡ ጋማ ፡ እንደለበሰ ፡ እየጋለበ ፡ እየገሰገሰ
ዘው ፡ ብሎ ፡ ገባ ፡ ጦር ፡ ሜደ ፡ መሃል
ፈረሱ ፡ እንደሆን ፡ ሰልፍን ፡ ይወዳል
ከት ፡ ብሎ ፡ ይስቃል ፡ በፍርሃት ፡ ላይ
አይመለሥም ፡ ጦርነት ፡ ሳያይ
እርሱ ፡ ግድ ፡ የለው ፡ ጭራሽ ፡ ይሮጣል
አይደነግጥ ፡ ኧረ ፡ እሰይ ፡ ይላል
ጦርነት ፡ ሽቶት ፡ ደስታ ፡ የሚሞላ
ከፈረስ ፡ በቀር ፡ ማን ፡ አለ ፡ ሌላ
ልክ ፡ እንደ ፡ ፈረስ ፡ የሚያስፈራ
ሰራዊት ፡ መጥቷል ፡ ኃይል ፡ የተሞላ

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ኃያላን ፡ መጡባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃያላን ፡ መጡላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታ ፡ ደረሰላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
እንደ ፡ ብርቱ ፡ ሕዝብ ፡ ያኮበኩባል
በሩን ፡ ብትዘጉ ፡ በመስኮት ፡ ይገባል
አንዱ ፡ ካንዱ ፡ ጋር ፡ ሳይገፋፋ
አንዱ ፡ በሌላው ፡ ሳይገፋፋ
መንገዱን ፡ ይዞ ፡ ቀጥ ፡ ብሎ ፡ ይሄዳል
በራሱ ፡ መንገድ ፡ ይጠበጥባል
በሰልፍ ፡ መሃከል ፡ በፍልሚያው ፡ ስፍራ
የራሱን ፡ ወገን ፡ ስለሚያጣራ
ተሳስቶ ፡ ረስቶ ፡ በወንድሙ ፡ ላይ
አይለውጠውም ፡ ለይቶ ፡ ሳያይ
ስለዚህ ፡ መቁሰል ፡ መሰነከካከል
በፍፁም ፡ የለም ፡ በእርሱ ፡ መሃከል

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ መጣላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ምህረት ፡ ወረደላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
ይሄ ፡ ሰራዊት ፡ በሰልፍ ፡ ሲያልፍባት
ዘንድሮስ ፡ ጉድ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ ፈርዶባት
ትናወጣለች ፡ ይህንን ፡ አይታ
በተራራው ፡ ላይ ፡ ኮቴውን ፡ ሰምታ
በእቅጥቃጤ ፡ ያናውጧቷል
እንቆቅልሿን ፡ ይፈቱላታል
እስራቷንም ፡ የሚበጣጥስ
ሰራዊት ፡ መጥቷል ፡ የሚገሰግስ
ባታምነው ፡ እንኪ ፡ አንተም ፡ እኮ ፡ አለህ
የዚህ ፡ ሰራዊት ፡ ዋነኛ ፡ አባል ፡ ነህ
አታውቂም ፡ እንጂ ፡ አንቺም ፡ እኮ ፡ አለሽ
የዚህ ፡ ሰራዊት ፡ ዋነኛ ፡ አባል ፡ ነሽ

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ እኛ ፡ መጣንባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ እኛ ፡ መጣላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ በዛላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ እኔ ፡ መጣሁላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
እጁን ፡ ሲጭን ፡ ደዌ ፡ ይፈወሳል
በስብከታቸው ፡ ሰው ፡ ይመለሳል
በትምህርታቸው ፡ የስህተት ፡ ትምህርት
ሊነቀል ፡ ??? ፡ ከስር ፡ ከመሰረት
ዝማሬንማ ፡ ከጀማመሩ ፡ መናፍስቶችን ፡ ያራውጣሉ
ጌታ ፡ መድሃኒት ፡ ስላደረጋቸው
ለምድሪቱ ፡ ፈውስ ፡ መፍትሄ ፡ አላቸው
ተረኛ ፡ አድርጐ ፡ ስለላካቸው
ለሰራተኞች ፡ ልቀቁላቸው
እኛ ፡ እንቢ ፡ ብንል ፡ ሊሆን ፡ ግድ ፡ ነው
የሰራዊቱ ፡ መሪ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃይለኞች ፡ መጡላት
ምድሬ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታዬ ፡ ጐበኛት
ምድሬ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣላት

ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው ፡ የመጣው
ምን ፡ ዓይነት ፡ ሰራዊት ፡ ነው (፪x)
አላማቸውን ፡ ለገንዘብ ፡ ሲሉ ፡ ለጥቅማጥቅም ፡ የማይደለሉ
ለያዙት ፡ እውነት ፡ ቆራጦች ፡ ናቸው
በፍፁም ፡ የለም ፡ የሚያስፈራቸው
ውስጣቸው ፡ በቃል ፡ ስለተሞሉ
ስራ ፡ እያላቸው ፡ ቁጭ ፡ የማይሉ
ቀልድና ፡ ተረት ፡ የማያወሩ
የሚሯሯጡ ፡ ወደ ፡ መከሩ
እነዚህ ፡ ናቸው ፡ ሰራተኞቹ
ለእግዚአብሔር ፡ ስራ ፡ ልብ ፡ አድርሶቹ
እነኛዎቹም ፡ አበቃላቸው ፡ ሰራዊቶቹን ፡ ጌታ ፡ አስነሳቸው

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ቆራጦች ፡ መጡባት
ምድር ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ ላከላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ መፍትሄ ፡ ተገኘላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ኃይለኞች ፡ መጡላት

ማነው ፡ የሰራዊቱ ፡ አለቃ
ማነው ፡ የሰራዊቱ (፪x)
የሰራዊቱ ፡ ዋና ፡ አለቃ
ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ትዕዛዝ ፡ አወጣ
ከፈተላቸው ፡ የምድሪቱን ፡ በር
ያለውን ፡ እርግማን ፡ እስኪሰባበር
እነርሱም ፡ ቆራጥ ፡ ወሳኞች ፡ ናቸው
የተሰማሩ ፡ በየድርሻቸው
ውስጣቸው ፡ ፀጋ ፡ ስለተሞሉ
ሲጠባበቁ ፡ እስካሁን ፡ አሉ
ከእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ እንኳን ፡ ቃል ፡ ወጥቶ
ተቁነጥኗል ፡ ውስጣቸው ፡ ሞልቶ
የልቡን ፡ ሃሳብ ፡ ሊፈጽሙ ፡ ነው
ዞር ፡ በሉላቸው ፡ ጊዜው ፡ የእነርሱ ፡ ነው

ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ሰራዊት ፡ መጣባት
ምድር ፡ ጉድ ፡ ፈላባት (፪x) ፡ ወሳኞች ፡ መጡባት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ልፍስፍስ ፡ ጠፋላት
ኢትዮጵያ ፡ አለፈላት (፪x) ፡ ወሳኞች ፡ መጡላት

"መጽሐፍ ፡ ቅዱስ ፡ ጥቅስ"