በእኔ ፡ ላይ (Benie Lay) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
በእኔ ላይ
ምህረቱ ነው የበላይ
ትርጉም አይገኝም ስለእርሱ ምህረት
ፈጽሞም አያልቅም ቢባል ቢባልለት
ልገልጸው አልችልም እኔም አቅቶኛል
በእኔ ላይ ምህረቱ እጅግ በዝቶልኛል
በእኔ ላይ
ምህረቱ ነው የበላይ
ከተወለድኩበት እስክ አሁን ቀን ድረስ
በዚህች በምድር ላይ ቆሜ ስመላለስ
በህይወቴ ዘመን የበዛው ጥበቃ
ነፍሴን አሳረፋት ምሳቀቋ በቃ
በእኔ ላይ
ጥበቃው ነው የበላይ
ለውድ ድር ብዬ ፍቅሩን አላቀርብም
የአምላክ ፍቅር ከሰው ምድቡም አይግጥምም
ይእርሱስ የተለየ መውደዱም ልዩ ነው
ብእኔ ላይ የበላይ የአምላኬ ፍቅር ነው
የኢየሱስ ፍቅር ነው
በእኔ ላይ
ፍቅሩ ነው የበላይ
ቆጥቦ ሰስቶ ወስኖ አይሰጠኝም
ቸር ነውና እርሱ ደጅ አያስጠናኝም
ለህይወቴ ዘመን የሚያስፈልገኝን
በኔ ላይ ይሞላል ቸር ነው አይነሳኝም
ቸር ነው አይነጥቀኝም
ብእኔ ላይ
ቸርነቱ ነው የበላይ
ከሞትና ሲዖል ወጣሁ ከሰቀቀን
በጣም ተደላደልኩ ጌታን ያገኘሁ ቀን
በህይወት መዝገብ ላይ ስሜን አሰፈረ
ሰይጣን ላያገኘኝ ዘላልም አፈረ ዘላለም ከሰረ
በእኔ ላይ
ማዳኑ ነው የበላይ
|