አቤቱ ፡ መተላለፌን ፡ ደምስሳት (Abietu Metelalefien Demsesat) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Lyrics.jpg


(Volume)

የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
(Ye11gnaw Seat Yetselot Teri)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

 
"አምላክ ፡ ሆይ ፡ ስለዘለዓለማዊ ፡ ፍቅርህ ፡ ይቅር ፡ በለኝ
ስለታላቁ ፡ ምህረትህም ፡ ኀጢአቴን ፡ ደምስስልኝ
በደለኔን ፡ ሁሉ ፡ አጥበህ ፡ አስወግድልኝ
ከኀጢአቴም ፡ አንጻኝ
እኔ ፡ ስህተቴን ፡ አውቃለሁ። የኀጢአቴንም ፡ ብዛት ፡ ዘወትር ፡ እገነአባለሁ
እኔ ፡ ያመጽኹት ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ነው
የበደልኹትም ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ ነው
አንተ ፡ የምትጠላውን ፡ ነገር ፡ አደረግኩ
ስለእዚህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ መፍረድህና ፡ እኔንም ፡ መቅጣትህ ፡ ትክክል ፡ ነው
ኀጢአተኛ ፡ ሆኜ ፡ እንደተወለድኩ ፡ ታውቃለህ
ከተጸነስኩበት ፡ ጊዜም ፡ ጀምሮ ፡ ኀጢአተኛ ፡ ነኝ
አንተ ፡ ቅንነትን ፡ እና ፡ እውነትን ፡ ስለምትወድ
የጥበብህን ፡ ሚስጥር ፡ አስተምረኝ
በህጾብ ፡ ቅጠል ፡ ረጭተህ ፡ ኀጢአቴን ፡ አስወግድልኝ ፡ እኔም ፡ እነጻለሁ
እጠበኝ ፡ እኔም ፡ ከበረዶ ፡ ይበልጥ ፡ ነጭ ፡ እሆናለሁ
የደስታንና ፡ የሃሴትን ፡ ድምጽ ፡ አሰማኝ
ምንም ፡ እንኳን ፡ ሰብረህ ፡ ያደቀከኝ ፡ ብሆንም
እንደገና ፡ ደስ ፡ አሰኘኝ
ኀጢአቴን ፡ አትቁጠርብኝ ፡ ከበደሌም ፡ አንጻኝ
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ንጹህ ፡ ልብ ፡ ፍጠርልኝ
አዲስና ፡ ታማኝ ፡ ሆኖ ፡ የሚጸና ፡ መንፈስ ፡ በውስጤ ፡ አኑርልኝ
ከፊትህ ፡ አታርቀኝ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህንም ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ
ከአዳኝነትህ ፡ የሚመነጨውን ፡ ደስታ ፡ መልሰህ ፡ ስጠኝ
እንድታዘዝም ፡ ፈቃደኛ ፡ አድርገኝ"

አዝ፦ አቤቱ ፡ እንደቸርነትህ ፡ ብዛት
እንደ ፡ ምህረትህ ፡ ብዛት
መተላለፌን ፡ ደምስሳት (፬x)

እኔ ፡ መተላለፌን ፡ አውቃለሁ
ከቶ ፡ አልክድም ፡ ፊትህ
በደሌም ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊትህ ፡ ነው
አንሳኝ ፡ በምህረትህ
እንድትመራኝ ፡ ብዬ ፡ መጣሁ
እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ ነጭ ፡ እሆናለሁ (፪x)

አዝ፦ አቤቱ ፡ እንደቸርነትህ ፡ ብዛት
እንደ ፡ ምህረትህ ፡ ብዛት
መተላለፌን ፡ ደምስሳት (፬x)

ለበደሌ ፡ ክርክር ፡ አላቀርብም
እኔ ፡ አልሟገትም
መናዘዝ ፡ እንጂ ፡ እያልኩኝ ፡ ኀጢአተኛ ፡ ነኝ
ሌላ ፡ ምን ፡ ምርጫ ፡ አለኝ
ስለዚህ ፡ በሂሶብ??? ፡ እርጨኝና
እጠበኝ ፡ ከበረዶ ፡ ይልቅ ፡ ነጭ ፡ እሆናለሁ (፪x)

አዝ፦ አቤቱ ፡ እንደቸርነትህ ፡ ብዛት
እንደ ፡ ምህረትህ ፡ ብዛት
መተላለፌን ፡ ደምስሳት (፪x)

"ጌታ ፡ ሆይ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህ ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ አትውሰድብኝ"

ቅዱስ ፡ መንፈስህን (፪x)
ከእኔ ፡ ላይ (፪x)
ኧረ ፡ አትውሰድብኝ
(፪x)

ቅዱስ ፡ መንፈስህን (፪x)
ከእኔ ፡ ላይ (፪x)
ኧረ ፡ አትውሰድብኝ
(፪x)

ታድያ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ይህን ፡ ታላቅ ፡ ስም ፡ ልጠራ
ታዲያ ፡ እኔ ፡ ማነኝ ፡ ፊትህ ፡ ለማቅረብ ፡ ምሥጋና
ግን ፡ ፊትህ ፡ ለመቆም ፡ ሞገስ/ምህረት ፡ ከአገኘሁ
ምሥጋናን ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ
ምሥጋናን ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ (፪x)

ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ለኢየሱስ ፡ ምሥጋና
ይገባሃል ፡ አምላክ ፡ ለአንተ
ለሆንከው ፡ ገናና (፪x)

"እግዚአብሔር ፡ መሃሪና ፡ ይቅር ፡ ባይ ፡ ነው
ከቁጣ ፡ የራቀ ፡ ምህረቱም ፡ የበዛ
ሁልጊዜ ፡ አይቀስፍም ፡ ለዘለዓለምም ፡ አይቆጣ
እንደኀጢአታችን ፡ አላደረገብንም ፡ እንደበደላችንም ፡ አልከፈለንም
ሰማይ ፡ ከምድር ፡ ከፍ ፡ እንደሚል ፡ እንዲሁ ፡ እግዚአብሔር
ምህረቱን ፡ በሚፈሩት ፡ ላይ ፡ አጠነከረ
ቸር ፡ እንደሆነ ፡ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ እንደሆነች
እግዚአብሔርን ፡ የሚፈሩ ፡ ሁሉ ፡ አሁን ፡ ይናገሩ"

ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x)
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x)
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x)
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x)
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x) ፣ ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነው (፬x)