የሙሽራው ፡ የሙሽሪት (Yemusheraw Yemusherit) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 7:28
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
"ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና
እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ
ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x)

እግዚአብሔር ፡ ቤትን ፡ ካልሰራ ፡ ሰው ፡ በከንቱ ፡ ይደክማል
መሰረቱ ፡ ግን ፡ የሆነ ፡ ቤቱ ፡ ይጸናል ፡ ይቆማል
ሁለትን ፡ ሰው ፡ አንድ ፡ የሚያደርግ ፡ ልዩ ፡ ችሎታ ፡ አለው
ይህ ፡ ዕውቀቱ ፡ አሰራሩ ፡ ለእኛ ፡ እጅግ ፡ አስደናቂ ፡ ነው

እድምተኞቻችን ፡ ብሉልን ፡ ጠጡልን ፡ ከሚሏቹህ ፡ ሌላ
ቃል ፡ አላቸው ፡ ዛሬ ፡ አክብሩልን ፡ ብለው ፡ የጌቶቹን ፡ ጌታ
ስንቱን ፡ አሳልፎ ፡ ቤት ፡ ለሰራላቸው ፡ ለዚህ ፡ መድሃኒያለም
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከዕልልታ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከጭብጨባ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከዝማሬ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም

አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
"ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና
እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ
ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x)

የታመነ ፡ አምላክ ፡ በእራሱ ፡ መንገዱ ፡ ያስተሳሰራቸው
ከአእምሮ ፡ በላይ ፡ በሆነው ፡ ጥበቡ ፡ ያገናኛቸው
ከፀሐይ ፡ በታች ፡ ባገኙት ፡ በዕድሜ ፡ ዘመኖቻቸው
ጌታ ፡ ይረዳናል ፡ እያሉ ፡ ጀመሩ ፡ ደስ ፡ እያላቸው

ዛሬን ፡ የደስታ ፡ ቀን ፤ የጥምረት ፡ የሃሴት ፡ ንጉሥ ፡ ካደረገው
ይህን ፡ አዲሱን ፡ ቤት ፤ ወዳጅ ፡ ቤተሰቦች ፡ አብረን ፡ እንመርቀው
ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው ፤ በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሞገስ ፡ ከሆነለት
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት

አዝ፦ የወንድ ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
የሴት ፡ ሙሸራ ፡ ድምጽ
"ቸር ፡ ነውና ፤ ቸር ፡ ነውና
ምህረቱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ነውና
እግዚአብሔርን ፡ አመስግኑ" ፡ ይላሉ
ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ ፤ ሙሽሮቹ ፡ ይላሉ (፪x)

ዛሬን ፡ የደስታ ፡ ቀን ፤ የጥምረት ፡ የሃሴት ፡ ንጉሥ ፡ ካደረገው
ይህን ፡ አዲሱን ፡ ቤት ፤ ወዳጅ ፡ ቤተሰቦች ፡ አብረን ፡ እንመርቀው
ሚስትን ፡ ያገኘ ፡ ሰው ፤ በረከት ፡ ካገኘ ፡ ሞገስ ፡ ከሆነለት
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት

ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከዕልልታ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከጭብጨባ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
ከዝማሬ ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ምሥጋና ፡ ይብዛለት
እንዲህ ፡ ላደረገው ፡ ጭብጨባ ፡ ይብዛለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ እስኪ ፡ ተቀኙለት
ይህን ፡ ላደረገው ፡ ዕልልታ ፡ ይብዛለት
ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ የሚሰጠው ፡ የለም