From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ገዢና ፡ ተገዢ ፡ መኳንንት ፡ ሹማምንት
የአገሬው ፡ ህዝብ ፡ ሁሉ ፡ የተሳተፉበት
እምቢልታ ፡ መሰንቆ ፡ በገናና ፡ ዋሽንት
ሁሉም ፡ ተሰለፎ ፡ ለአንድ ፡ ሰው ፡ ትዕቢት
አቤት ፡ ትዕቢት (፪x) ፡ የአንድ ፡ ንጉሥ ፡ ትዕቢት
አገር ፡ ሲያሰግድ ፡ ህዝቡን ፡ ሲያንቀጠቅጥ
ሶስት ፡ ደፋር ፡ ሰዎች ፡ ጣዖት ፡ ያለመዱ
አንሰግድም ፡ ሲሉ ፡ በዓል ፡ አበላሹ
ንጉሡም ፡ ሲሰማ ፡ በትዕቢት ፡ ተቆጣ
እቶኑን ፡ ጨመረው ፡ እጥፍ ፡ እንዲነድ ፡ ሌላ
ጉድ ፡ ፈላ
አንሰግድም ፡ ያሉ ፡ በትዕቢት ፡ በጋለ ፡ እቶን ፡ ውስጥ ፡ ተጣሉ
ወድቀው ፡ ተቃጥለው ፡ አረው ፡ ተኮማትረው
መች ፡ ቀሩ ፡ መች ፡ ቀሩ ፡ ምንም ፡ ቢታሰሩ
ተፈታ ፡ ገመዱ ፡ እያለ ፡ አዳኙ
ጭራሽ ፡ ወዲህ ፡ ወዲያ
ይራመዱ ፡ ጀመር ፡ የተስማማ ፡ እስኪመስል
እንዴትስ ፡ አይመች ፡ እንዴትስ ፡ አይድላ ፡ ኢየሱስ ፡ ካለማ (፪x)
ትዕቢቱ ፡ ተመታ ፡ የንጉሡ ፡ ሲበለሻሽበት ፡ ድግሱ
ሶስት ፡ ሰዎችን ፡ ጥሎ ፡ አራት ፡ ሲሆኑበት
ነገር ፡ ግራ ፡ ሆነበት
ንጉሱም ፡ እንዲህ ፡ አለ ፡ አዋጁን ፡ ቀየረ
እየደነገጠ ፡ እነዚያን ፡ ብሩካን ፡ አውጧቸው ፡ ከእሳት
እናምልከው ፡ በቃ ፡ የእነርሱን ፡ አምላክ (፪x)
ሁሉም ፡ ሰው ፡ ያምልከው ፡ ይስገድለት ፡ ፊቱ
ያስደንቃልና ፡ የማዳን ፡ ጉልበቱ ፡ እንደፋ ፡ ፊቱ
እስቲ ፡ ጐምበስ (፪x) ፡ ይባልለት ፡ ይሰገድለት
እስቲ ፡ ጐምበስ (፪x) ፡ ይባልለት ፡ ይሰገድለት
አያልቅበት (፪x) ፡ ማዳኑ ፡ አያልቅበት
አያልቅበት ፡ መታደጉ ፡ አያልቅበት
አያልቅበት ፡ ምህረቱ ፡ አያልቅበት
እስቲ ፡ ጐምበስ (፪x) ፡ ይባልለት ፡ ይሰገድለት
እስቲ ፡ ጐምበስ (፪x) ፡ ይባልለት ፡ ይሰገድለት (፪x)
|