ፍቅርህ ፡ ትልቅ ፡ ነው (Feqereh Teleq New) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው
(Barkotien Lequterew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 6:16
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)

ጸሃፊ ፡ መች ፡ ጠፍቶ
በምድር ፡ ላይ ፡ ምሁር ፡ ሰው
የአንተን ፡ ታላቅነት ፡ ጀምሮ ፡ አይጨርሰው
መች ፡ አንዲህ ፡ ይቀላል ፡ ስለአንተ ፡ ቢባል ፡ ቢባል
ቢጻፍልህ ፡ ተጀመሮ ፡ ቀለም ፡ ያልቃል

እኔ ፡ ግን ፡ አድናቆቴን ፡ ለአንተ
ባለኝ ፡ በሰጠኸኝ ፡ ዜማ
ማወደሴን ፡ ማክበሬን ፡ አልተውም
ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ እስኪሰማ
ጌታዬ ፡ ጌታዪ ፡ ነህ ፡ እያለኩ
ቤትህ ፡ ቆሜ ፡ እንጓደዳለሁ
ኧረ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ እኮ ፡ ለእኔ
እንደአንተ ፡ የት ፡ አገኛለሁ

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)

ስለአንተ ፡ ክብር ፡ ስልጣን ፡ ሞገስ ፡ ማንነት
እየተረከ ፡ ነው ፡ ይኼ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት
ይህ ፡ ነው ፡ እስከዛሬ ፡ ከፍጥረት ፡ ጀምሮ
አላለቀበትም ፡ ስለአንተ ፡ ተናግሮ

አቤት ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ፡ እሄ
ሁሉ ፡ ምሥጋናና ፡ ስግደት
ያለማቋረጥ ፡ ያጐርፍልሃል ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ከያለበት
እኔም ፡ ተረኛ ፡ ነኝ ፡ ለአንተ ፡ ዛሬ
ፊትህ ፡ ለማቅረብ ፡ ምሥጋና
ጌታዬ ፡ ጌታዪ ፡ ነህ ፡ እያልኩኝ
ልቀኝልህ ፡ እንደገና

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)

እስከ ፡ ዛሬ ፡ ስለአረክልኝ ፡ ውለታ
አቀርብልህ ፡ ነበር ፡ ምሥጋናና ፡ እልልታ
ስለአረክልኝ ፡ አይደለም ፡ ምቀኝልህ
ስለደነቀኝ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ ማንነትህ

ተገረምኩ ፡ አድናቆት ፡ ያዘኝ ፡ በአንተ
ማንነትህን ፡ አውቄ
እስቲ ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ ፡ ልበል
በእግሮችህ ፡ ስር ፡ ወድቄ
ቃላት ፡ ያንሰኛል ፡ ለመግለጽ ፡ የአንተን
ማንነትህ ፡ ወደር ፡ የለው
. (1) . ፡ ፍቅርህ
ስምህ ፡ ምሥጋና ፡ ይድረሰው

አዝ፦ ፍቅርህ ፡ ጥልቅ ፡ ነው (ጌታዬ)
ምህረትህ ፡ ብዙ (ጌታዬ)
ቸርነትህ ፡ አያልቅ (ጌታዬ)
አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (ጌታዬ)
ስራህ ፡ ግሩም ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ጌታዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ባለውለታዬ/አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)