From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
በአለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)
ቤቴ ፡ አሸዋ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
እስከአሁን ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ ችግርም ፡ አላየሁ
በጋው ፡ ተስማምቶኛል ፡ ምን ፡ ችግር ፡ ይመጣል
ውኃ ፡ እኮ ፡ በአሸዋ ፡ ወዲያው ፡ ይመጠጣል
"መስሎሃል"
ይልቅ ፡ ወጪ ፡ አታውጡ ፡ አለት ፡ አትቧጥጡ
ወጪን ፡ ይቀንሳል ፡ አሸዋ ፡ እኮ ፡ ሞልቷል
የእኔስ ፡ ቤት ፡ አምራለች ፡ በጣም ፡ ዘንጣለች
ላለሁበት ፡ ጊዜ ፡ ተመችታኛለች
"ተው ፡ ይቅርብህ"
አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
ክረምት ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ዝናብ ፡ የመጣ ፡ ቀን
ጐርፉ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ንፋስ ፡ የመጣ ፡ ቀን
ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር
ገንዘብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
ዕውቀትህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
ሥልጣንህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
ጥበብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት
ችግር ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ሃዘን ፡ የመጣ ፡ ቀን
መከራ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ማጣት ፡ የመጣ ፡ ቀን
ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
ባለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x)
ቤቴ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው
ችግሩም ፡ በሽበሽ ፡ ነው ፡ መከራብ ፡ ብዙ ፡ ነው
ጐርፉ ፡ ሲወርድብኝ ፡ ነፋስ ፡ ሲነፍስብኝ
አለት ፡ ላይ ፡ ስላለሁ ፡ ቤቴ ፡ አልፈረሰብኝ
"ኧረ ፡ ምንም ፡ አትሆን"
አለት ፡ በቀላሉ ፡ አይገኝም ፡ ሲሉ
የምደክም ፡ መስሎኝ ፡ ድሮ ፡ ተሞኘሁኝ
የአሸዋ ፡ ነጋዴው ፡ ነበርና ፡ ወሬው
ቤቴን ፡ በዓለት ፡ ብቻ ፡ ሰራሁ ፡ ከነአካቴው
"ደግ ፡ አድርገሃል"
አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት
አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት
በቃ ፡ አለፈለት (፪x)
ክረምቱ ፡ ቢመጣ ፤ ዝናቡም ፡ ቢወርድ
ጐርፉ ፡ ቢንደረደር ፤ ንፋሱም ፡ ቢነፍስ
የአንተ ፡ ቤት ፡ እንደሆን ፡ ፈጽሞ ፡ አይላወስ
ኢየሱስ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
ቃሉ ፡ ከሆነልህ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት
በቃ ፡ አለፈለት (፪x)
መከራ ፡ ቢመጣ ፤ ችግር ፡ ቢደርስብህ
ሃዘን ፡ ቢያጋጥምህ ፤ ማጣት ፡ ቢያስቸግርህ
አትነቃነቅም ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ስላለህ
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ
በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ
በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)
|