አባትነት ፡ ከሚሰየምበት (Abatenet Kemiseyemebet) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit 2006.jpeg

፳ ፻ ፮
(2006)

የ፲፩ኛው ፡ ሰዓት ፡ የጸሎት ፡ ጥሪ
(Ye11gnaw Seat Yetselot Teri)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፰ (2006)
ቁጥር (Track):

(5)

ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

ስለዚህ ፡ ምክንያት ፡ በሰማይና ፡ በምድር ፡ ያለ
አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ከአብ ፡ ፊት ፡ እምበረከካለሁ

አዝ፦ አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)
አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)

የሕይወቴንና ፡ የኑሮዬን ፡ ሸክም
ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ ይዤው ፡ አልመላለስም
ጠዋት ፡ ተነስቼ ፡ ስደፋ ፡ በፊቱ
ሸክሜ ፡ ተራግፎልኝ ፡ እሆናለሁ ፡ ብርቱ
ያለምክንያት ፡ አይደል ፡ የምምበረከከው
ሰምቶ ፡ የሚመልስ ፡ አምላክ ፡ ስላለኝ ፡ ነው
(፪x)

አዝ፦ አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)
አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)

ያለኝን ፡ የልቤን ፡ ለማውራት ፡ በፊቱ
ከእግሩ ፡ በቀር??? ፡ ስሆን ፡ ይመጣል ፡ መንፈሱ
መልስ ፡ እንኪመጣልኝ ፡ በፊቱ ፡ ያለእረፍት???
መንፈሱ ፡ ያግዘኛል ፡ ከልቤ??? ፡ እንድቃትር???
አምናለሁ ፡ ይራገፋል ፡ በእኔ ፡ እያለው ፡ ሸክም
በፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ያለ ፡ መልስ ፡ አልሄድም
(፪x)

አዝ፦ አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)
አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)

አባቴ ፡ ነውና ፡ ይሰማኛል ፡ ብዬ
ልጠይቅ ፡ ልረዳ ፡ ያለኝን ፡ ከልቤ
ፊቱ ፡ ስንበረከክ ፡ ደስታን ፡ አሞላለሁ
ለጠየቅሁት ፡ ሁሉ ፡ መልስን ፡ አገኛለሁ
እንዲሁ ፡ አይደለም ፡ በፊቱ ፡ መውደቄ
ማንነቱን ፡ በደምብ ፡ ገብቶኝ ፡ ነው ፡ አውቄ
(፪x)

አዝ፦ አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)
አባትነት ፡ ሁሉ ፡ ከሚሰየምበት ፡ ዙፋንህ ፡ ካለበት
እምበረከካለሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ይታጠፋል ፡ ሸክሜ ፡ ይራገፋል (፪x)

ተነስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ስራ ፡ እንደቀድሞ
ይብቃ ፡ ይህ ፡ ድካሜ ፡ ይወገድ ፡ ፈጽሞ
ከከበበኝ ፡ ነገር ፡ መፍትሄ ፡ እንድትሆነኝ
ወደ ፡ አንተ ፡ እጣራለሁ ፡ ኢየሱሴ ፡ ምትሰማኝ

ልጥራህ ፡ በማለዳ ፡ ልጥራህ ፡ በጠዋቱ (፪x)
ዛሬም ፡ ምታድሰኝ ፡ ኢየሱስ ፡ የናዝሬቱ
ኢየሱስ ፡ የጥንቱ (፪x)