እንመርቃቹሃለን (Enmereqachuhalen) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

 
በስመአብ ፡ ወወልድ ፡ ወመፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አንድ ፡ አምላክ
ይሄ ፡ ጋብቻ ፡ የተባረከ ፡ ጋብቻ ፡ ይሁንልን ፡ አሜን

አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ
በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x)

በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ
ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x)

ክርስቶስ ፡ እርሱ ፡ የሆነው ፡ መሰረት
እራስ ፡ ሆኖ ፡ ይንገሥበት ፡ እዚህ ፡ ይግባልን??? ፡ ቸርነት
ትዳሩም ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ተመርቶ
የባርኮት ፡ ሽታ ፡ ሸቶ ፡ በምሳሌነት ፡ ተሞልቶ
ከድግስ ፡ ያለፈ (አዎ) ፡ በሕይወታቸው ፡ ጉዞ (አዎ)
ይምራቹህ ፡ እጃችሁን ፡ ይዞ

አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ
በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x)

በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ
ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x)

ቤተሰብ ፡ ጤናማ ፡ ቤተክርስቲያን
ያድርጋት ፡ እንደብርሃን ፡ በፀጋው ፡ ብዛት ፡ ለማዳን
የደስታ ፡ ምንጭ ፡ ሆኖ ፡ ይፍለቅለቅበት
የተጠሙም ፡ የሚረኩበት ፡ ያዘኑም ፡ የሚደሰቱበት
እግዚአብሔር ፡ አዘዘ (አዎ) ፡ ጋብቻ ፡ እንዲከበር (አዎ)
ከጥንቱም ፡ ልክ ፡ እንደዚህ ፡ ነበር

ቃልኪዳን ፡ አላቹህና ፡ ከእግዚአብሔር
ብዙ ፡ ተባዙ ፡ ተባልን ፡ የአምላካቹህ ፡ ባርኮት ፡ ነው
ውለዱ ፡ ክበዱ ፡ ይሁን ፡ ደስታ
በፍቅር ፡ አምላክ ፡ በጌታ ፡ በሕይወታችሁ ፡ አለኝታ
እግዚአብሔር ፡ ያኖራል (አዎ) ፡ መኖሪያቹህ ፡ ሆኖ (አዎ)
ማን ፡ አፍሯል ፡ በእርሱ ፡ ተማምኖ

አዝ፦ አዲስ ፡ ኑሮ ፡ አዲስ ፡ ቤት ፡ አሃዱ ፡ የተባለው ፡ ዛሬ
በመልካም ፡ እንዲዘልቅ ፡ ይህ ፡ የፍቅር ፡ ጅማሬ
እንመርቃቹሃለን ፡ አሜን (፮x)

በአብ ፡ በወልድ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ
ተባረኩ ፡ ብለን ፡ እንመርቃቹሃለን (፪x)