ሙሽሪት ፡ ሙሸራው (Musherit Musheraw) - ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት
(Getayawkal & Birucktawit)

Lyrics.jpg


(5)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(6)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal & Birucktawit)

አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ
ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው
ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ

(አሜን) ፡ ልዑል ፡ አሰናዳ ፤ (አሜን) ፡ ባርኮት ፡ የሚበላ
(አሜን) ፡ ከማመስገን ፡ በቀር ፤ (አሜን) ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ሌላ
(አሜን) ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፤ (አሜን) ፡ ወደ ፡ እረፍት ፡ አመጣን
(አሜን) ፡ ከብቸኝነቱ ፤ (አሜን) ፡ መንደር ፡ እያወጣ

አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ
የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ
ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው
ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ

(አሜን) ፡ አክሊል ፡ የለበሰ ፤ (አሜን) ፡ ሙሽራው ፡ ሲያምርበት
(አሜን) ፡ በጌጥ ፡ ሽልማቷ ፤ (አሜን) ፡ ሙሽሪት ፡ ሲያምርባት
(አሜን) ፡ ነገር ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፤ (አሜን) ፡ ጽድቅን ፡ አጐናጽፎ
(አሜን) ፡ ሰውን ፡ ለዚህ ፡ ያበቃል ፤ (አሜን) ፡ ሁሉን ፡ አሳልፎ

አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ
የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ
ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው
ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ

አዲስ ፡ ጐጆ ፡ ወጪ ፡ በይ ፡ ባርኮቱን ፡ ጠጪ
ብሎ ፡ የመረቃት ፡ ደጉ ፡ ቸሩ ፡ አባት
እረድቷት ፡ አምላኳ ፡ ሲለወጥ ፡ ታሪኳ
ጐጆን ፡ ማን ፡ አስወጣት ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ያገዛት (፪x)

ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ የጌታ
በእርሱ ፡ ተጀምሯል ፡ የሙሽሪት ፡ ቤቷ (፬x)

አዲስ ፡ ስፍራ ፡ ሰጥቶ ፡ በኑሮም ፡ ገብቶ
ጌታ ፡ አደላደለው ፡ ተመስገን ፡ አስባለው
ይህን ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ስላሳየን ፡ ይክበር
ቃሉን ፡ ላላጠፈው ፡ ምሥጋናችን ፡ ይሄው (፪x)

ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ
በእርሱ ፡ ተጀምሯል ፡ የሙሽራው ፡ ቤቱ (፬x)

(አሜን) ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ እስከሞት ፤ (አሜን) ፡ ብርቱ ፡ ስለሆነ
(አሜን) ፡ እርሷም ፡ ለእርሱ ፡ ሆነች ፤ (አሜን) ፡ እርሱም ፡ ለእርሷ ፡ ሆነ
(አሜን) ፡ ጌታ ፡ ያነደደውን ፤ (አሜን) ፡ የፍቅርን ፡ እሳት
(አሜን) ፡ ብዙ ፡ የጥፋት ፡ ውኃ ፤ (አሜን) ፡ አይችልም ፡ ሊያጠፋት

አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ
የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ
እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ
ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው
ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ