ለጌታ ፡ አስፈልገዋለው (Legieta Asfelegewalehu) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው
(Barkotien Lequterew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 7:06
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝ፦ ለጌታ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለአምላኬ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለቤቱ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለስራው ፡ አስፈልገዋለው (፬x)

የመጨረሻውን ፡ ስራውን ፡ ልሰራ
የወንጌሉን ፡ መልዕክት ፡ ለዓለም ፡ እንዳበራ
የማብቂያውን ፡ ስራ ፡ ልጨርስ ፡ ልፈጽም
በምድር ፡ ሁሉ ፡ ዙሪያ ፡ ያለ ፡ እኔ ፡ አይሄድም
ያለ ፡ እኔ (፫x) ፡ አይሄድም

አዝ፦ ለጌታ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለአምላኬ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለቤቱ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለስራው ፡ አስፈልገዋለው (፬x)

በእኔ ፡ ላይ ፡ ተሳፍሮ ፡ ሲሄድ ፡ በመንገድ ፡ ላይ
የከበረው ፡ ጌታ ፡ ተቀምጦ ፡ ላዬ ፡ ላይ
ላይ ፡ ላይ ፡ ተቀምጦ ፡ ላዬ ፡ ላይ
ጨርቅና ፡ ዘንበባ ፡ ለእርሱ ፡ የተነጠፈው
ላዬ ፡ ላይ ፡ ስላለ ፡ . (1) . ፡ እንድረግጠው
የእርሱ ፡ እግር ፡ ሲረግጠው (፫x)
እኔም ፡ የምረግጠው

አዝ፦ ለጌታ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለአምላኬ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለቤቱ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
ለስራው ፡ አስፈልገዋለው (፬x)

አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ከታሰርኩበት ፡ እፈታለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ከተኛሁበት ፡ እነቃለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ከተኛሁበት ፡ እነቃለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ወደ ፡ ቦታዬ ፡ እመለሳለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ከበሽታዬ ፡ እፈወሳለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ ስለዚህ ፡ ከሸለቆዬ ፡ እወጣለሁ
አስፈልገዋለሁ ፡ አዎ ፡ አስፈልገዋለሁ ፡ አሜን (፬x)

ተቀምጦ ፡ በላዬ ፡ በምድር ፡ ዙሪያ ፡ በአደባባይ ፡ ላይ
ይሄዳል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይሰራል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይፈታል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይሰብካል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይዘምራል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይመራል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ያጽናናል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይፈውሳል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ያድናል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
ይታያል ፡ ጌታዬ (ተቀምጦ ፡ በላዬ)
በላዬ ፡ በላዬ ፡ ተቀምጦ ፡ በላዬ (፪x)

ይታያል ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ በእኔ ፡ ላይ
በላዪ ፡ ላይ ፡ በምድር ፡ ሁሉ ፡ ዙሪያ ፡ በየአደባባይ
ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ (፫x)
ይታያል ፡ ጌታዬ ፡ እኔን ፡ በልጦ
አዎ ፡ በልጦ ፡ በልጦ (፫x)

አዝ፦ ለጌታ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
(ለአምላኬ) ለአምላኬ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
(ለቤቱ) ለቤቱ ፡ አስፈልገዋለው (፬x)
(ለስራው) ለስራው ፡ አስፈልገዋለው (፬x)