ይቅርታ (Yeqerta) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ህጻናት ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጡ
(Hetsanat Wede Enie Yemtu)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 3:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

"ማሜ ፡ አሁን ፡ እኮ ፡ ያለሽ ፡ እድል
አባትሽህን ፡ ሄዶ ፡ ይቅርታ ፡ መጠየቅ ፡ ነው ።
አዎ ፡ አውቃለሁ ። እንዴ ፡ ግን ፡ እኔ ፡ ይቅርታ ፡ እጠይቀዋለሁ?

እንዴ ፡ ለምንድን ፡ ነው ፡ ሄደሽ ፡ ይቅርታ ፡ ማትጠይቄው?
መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ እኮ ፡ ስለይቅርታ
በጣም ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ የሚያስተምረን ።

አዎ ፡ አውቃለሁ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ የሚያስተምረን ።
ግን ፡ እኮ ፡ አንዳንዴ ፡ አውቄ ፡ አጠፋለሁ ።
አንዳንዴ ፡ ደግሞ ፡ ሳላውቅ ፡ አጠፋለሁ
እየተሳሳትኩኝ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የተሸገርኩት ።

አይ ፡ ልክ ፡ አይደለሽም ።
አሁን ፡ ቀስ ፡ ብለሽ ፡ ሂጂና ፡ ይቅርታ ፡ መጠየቅ ፡ አለብሽ
እንደተቀመጠ ፡ ቀስ ፡ ብለሽ ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ ሄደሽ ፡ ይቅርታ ፡ ጠይቂ ።
ወይኔ ፡ ጉዴ ፡ እፈራለሁ ፡ እኮ ።
እንዳይገርፈኝ ፡ ብዬ ፡ እኮ ፡ ፈርቼ ፡ ነው ።
አትፍሪ ፡ አይዞሽ ። ሂጂ ፡ ሂጂ ፡ አይዞሽ ፡ አትፍሪ ።"

ስለተሳሳትኩኝ ፡ ስላጠፋሁት
አውቄም ፡ ሳላውቁም ፡ ሁሉ ፡ ላረኩት
ጥፈተኝነቴ ፡ ገብቶኝ ፡ ይኸው ፡ ወጥቻለሁና
ድጋሜ ፡ አላጠፋም ፡ ለዛሬም ፡ ይቅርታ (፪x)

ይቅርታ (፪x) ፡ ይቅርታ (፬x)
ይቅርታ (፪x) ፡ ይቅርታ (፬x)

ያጠፋሸው ፡ ጥፋት ፡ በሙሉ ፡ ገብቶሻል
ቶሎ ፡ ብለሽ ፡ መጥተሽ ፡ ይቅርታ ፡ ብለሻል
ድጋሚ ፡ አታጥፌ ፡ እንጂ ፡ ልጄ
እኔም ፡ በጣም ፡ እወድሻለሁ
ነይ ፡ ልሳምሽ ፡ አንዴ ፡ ይቅር ፡ ብዬሻለሁ

I love you (እወድሻለሁ) (፮x)
I love you (እወድሻለሁ) (፮x)