ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (Qal Becha Tenager) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ባርኮቴን ፡ ልቁጠረው
(Barkotien Lequterew)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ (2008)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 9:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

አዝቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x)
የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x)
ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x)

የታመመብኝን ፡ ሰው ፡ አልጋ ፡ ላይ ፡ አስተኝቼ
ወደ ፡ አንተ ፡ መጣሁኝ ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ትቼ
ቃልህ ፡ ዓይን ፡ እንዳለው ፡ ስለተማመንኩኝ
መቅደስህ ፡ ገብቼ ፡ ቃልህን ፡ ጠበኩኝ
ተነሳ ፡ ከአልጋ ፡ ላይ ፡ ብለህ ፡ እዘዝልኝ
ወዲያው ፡ እንደሚነሳ ፡ በቃል ፡ አምናለሁኝ (፪x)

አዝቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x)
የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x)
ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x)

ለሰው ፡ ያልነገርኩት ፡ ማንም ፡ የማያውቀው
እንድ ፡ ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ አንተ ፡ የምታውቀው
አምላክ ፡ ይቻልሃል ፡ ለአንተ ፡ ሁሉ ፡ ነገር
ለችግሬ ፡ መውጫ ፡ ስለአዘጋጀህ ፡ በር
እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ልሸከም ፡ ጥያቄ
ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናግረህ ፡ ፍታ ፡ እንቆቅልሼን (፪x)

አዝቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x)
የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x)
ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x)

እኔ ፡ የቀመስኩትን ፡ ሕይወት ፡ ያልቀመሱ
በምስራች ፡ ወንጌል ፡ ገና ፡ ያልተደረሱ
በቤቴ ፡ ሞልተዋል ፡ አንተን ፡ ያልተረዱ
ወደ ፡ ሞት ፡ ጐዳና ፡ ዝምብለው ፡ ሚነዱ
ዛሬ ፡ ቃል ፡ ተነገር ፡ እንዲለወጡልኝ
ቤቴ ፡ ወንጌል ፡ ይግባ ፡ አንተን/ጌታን ፡ ያግኙልኝ (፪x)

አዝቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x)
የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x)
ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x)

ሰማይና ፡ ምድርን ፡ በቃልህ ፡ አጽንተሃል
ሁኑ ፡ ስትል ፡ ሆነው ፡ በአንተ ፡ ተፈጥረዋል
ቃልህ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው ፡ ስልጣን ፡ የተሞላ
ሰይጣንን ፡ የሚጥል ፡ እሳት ፡ ነው ፡ ሚባላ
በሕይወቴ ፡ ዘመን ፡ የሚያስቸግረኝን
ቃል ፡ ብቻ ፡ ተናግረህ ፡ ጠላቴን/ሰይጣንን ፡ ጣልልኝ (፪x)

አዝቃል ፡ ብቻ ፡ ተናገር (፬x)
የአንተ ፡ ቃል ፡ ተራሮችን ፡ ዘሎ ፡ ይመጣል (፫x)
ቃል ፡ ብቻ ፡ ስትናገር ፡ ያልከው ፡ ይሆናል (፫x)

ደረቁን ፡ ምድረበዳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ይሞላዋል ፡ በአበባ ፡ ምን ፡ ተስኖት
የጐደለንን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ያደርግልናል ፡ ሙሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ለእርሱ ፡ የሚያቅት ፡ የለም
ይችላል ፡ እርሱ ፡ ዘለዓለም
ሁሉንም ፡ ቻይ ፡ ነውና
እናንግሰው ፡ በምሥጋና (፪x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)

የሞተውን ፡ ሬሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
እናያለን ፡ ሲያስነሳ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ለእኛ ፡ ያቃተን ፡ ሁሉ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ይቻለዋል ፡ በእርሱ ፡ ምን ፡ ተስኖት
ኤልሻዳይ ፡ አምላክ ፡ ነውና
የሚሳነው ፡ የለምና
ምን ፡ ተስኖት ፡ እንበለው
ድል ፡ የሚገኘው ፡ ያኔ ፡ ነው (፪x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)
ምን ፡ ተስኖት (፬x)