አብሬ ፡ ጨመሬ (Aberie Chemerie) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Getayawkal and Birucktawit Esp.jpg

ልዩ ፡ እትም
(Esp)

እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ
(Enkuan Des Alachehu)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:42
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

 
አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው
ላክብረው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ
አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x)

አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x)
እውነት ፡ የሆናቸው ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፪x)
ሞገስ ፡ የሆናቸው ፡ ኢየሱስ ፡ አይደለም ፡ ወይ (፪x)

አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x)
በስራና ፡ በቃል ፡ ብርቱ ፡ የሆነው ፡ ጌታ
እጃቸውን ፡ ይዞ ፡ ሁሌ ፡ እያበረታ
ለዚህ ፡ ላበቃቸው ፡ ስንቱን ፡ እየመታ
እዚህ ፡ አደረሳቸው ፡ ክፉን ፡ እየመታ

ቃል ፡ የገቡት ፡ ቤተሰቦቹ (፫x)
ከሁሉም ፡ ሚበልጥ ፡ አግኝቷል ፡ እጁ (፫x)
ቃል ፡ የገቧት ፡ ቤተሰቦቿ (፫x)
ወሰነች ፡ ልትኖር ፡ ከባሏ ፡ ብቻ (፫x)

ቤተሰብ ፡ ጓደኛ ፡ ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ሁሉ
በሰርጉ ፡ ያላችሁ ፡ ተጋባዥ ፡ በሙሉ
ላጤነት ፡ አብቅቶ ፡ ብቸኝነታቹህ
በቃ ፡ ለቀው ፡ ሄዱ ፡ ከቀድሞ ፡ ቀያቸው
አመስግኑ (ኦሆ) ፡ አጨብጭቡ (አሃ)
ለአምላካችሁ (ኦሆ) ፡ እልል ፡ በሉ (አሃ)
(፪x)

አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው/ላንግሰው
ላክብረው/ላንግሰው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ
አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x)

ከመጀመሪያው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ አንድን ፡ ወንድ ፡ ለአንድ ፡ ሴት ፡ አድርጐ ፡ ሰራው (፬x)
ከመጀመሪያው (፫x)
እግዚአብሔር ፡ አንድን ፡ ሴት ፡ ለአንድ ፡ ወንድ ፡ አድርጐ ፡ ሰራት (፬x)
ይህ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ዛሬም ፡ ይህ ፡ ነው (፬x)
ይህ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ፈቃድ ፡ ዛሬም ፡ ይህ ፡ ነው (፬x)

አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x)
በስራና ፡ በቃል ፡ ብርቱ ፡ የሆነው ፡ ጌታ
ሁሉን ፡ አሳመረ ፡ እጁ ፡ አለበት
ይሄው ፡ አሳመረው ፡ ቃሉ ፡ አለበታ
የቃል ፡ ኪዳን ፡ አምላክ ፡ ክንዱ ፡ አለበት

አላማሩም ፡ ወይ ፡ ዛሬ ፤ አላማሩም ፡ ወይ (፪x)
እርሱ ፡ ያገናኘውን ፡ ሰው ፡ አይለየውማ
ማጣመር ፡ ለሚችል ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዜማ
ሰው ፡ ማድረግ ፡ ለሚችል ፡ ምሥጋናን ፡ ላሰማ
መባረክ ፡ ለሚችል ፡ ዕልልታን ፡ ላሰማ

ቃል ፡ የገቡት ፡ ቤተሰቦቹ (፫x)
ከሁሉም ፡ ሚበልጥ ፡ አግኝቷል ፡ እጁ (፫x)
ቃል ፡ የገቧት ፡ ቤተሰቦቿ (፫x)
ወሰነች ፡ ልትኖር ፡ ከባሏ ፡ ብቻ (፫x)

ቤተሰብ ፡ ጓደኛ ፡ ዘመድ ፡ አዝማድ ፡ ሁሉ
በሰርጉ ፡ ያላችሁ ፡ ተጋባዥ ፡ በሙሉ
ላጤነት ፡ አብቅቶ ፡ ብቸኝነታቹህ
በቃ ፡ ለቀው ፡ ሄዱ ፡ ከቀድሞ ፡ ቀያቸው
አመስግኑ (ኦሆ) ፡ አጨብጭቡ (አሃ)
ለአምላካችሁ (ኦሆ) ፡ እልል ፡ በሉ (አሃ)
(፪x)

አዝ፦ እኔም ፡ ይህን ፡ ጌታ ፡ ላክብረው/ላንግሰው
ላክብረው/ላንግሰው ፡ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አብሬ
አብሬ ፡ ምሥጋናን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ዕልልታን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ አምልኮን ፡ ጨምሬ
አብሬ ፡ ጭብጨባን ፡ ጨምሬ (፪x)