ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቅ (Lejie Hoy Qalien Tebeq) - ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ
(Getayawkal and Birucktawit)

Lyrics.jpg


()

ህጻናት ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጡ
(Hetsanat Wede Enie Yemtu)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 2:46
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የጌታያውቃል ፡ ግርማይ ፡ እና ፡ ብሩክታዊት ፡ አሰፋ ፡ አልበሞች
(Albums by Getayawkal and Birucktawit)

"ሚጡ ፡ ሚጡ ፡ ነይና ፡ አባባ ፡ እንቅልፋቸው ፡ ሳይመጣ
ምከሩን ፡ እንበላቸው ፡ እንደትላንትና ።
ውይ ፡ እኔ ፡ እኮ ፡ በጣም ፡ ነው ፡ ምወደው ፡ የሳቸውን ፡ ምክር ።
እሺ ፡ ነይ ፡ ደስ ፡ ይለኛል

አባባ ፡ አባባ? ምክር ፡ ምከሩን ፡ አባባ ።
ምክር ፡ አላችሁ? አዎ ፡ አዎ ።
እሺ ፡ እስቲ ፡ ዛሬ ፡ እስኪ ፡ ደግሞ ፡ ከምሳሌ ፡ መጽሃፍ
እስቲ ፡ አንድ ፡ ምክር ፡ ልምከራቹህ ። አሺ ፡ እሺ ።

እንደዚህ ፡ ይላል ፡ ልጆቼ ።
ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቅ
ትዕዛዜንም ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽግ
ትዕዛዜንም ፡ ጠብቅ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖራለህ ፡ ያላል ።

የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ ስትጠብቁ ፡ በሕይወት ፡ ትኖራላችሁ ፡ እሺ?
እሺ! ፡ ጐበዝ ፡ ልጆች ።
እስቲ ፡ እቼን ፡ መዝሙር ፡ ደስ ፡ እያላችሁ ፡ ዘምሯት ።
እሺ ፡ አባባ ፡ ሚጡ ፡ ነይ!
ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ስጠኝ ፡ እያላችሁ ፡ አምላክን ፡ ለምኑት ።"

ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቅ
ትዕዛዜንም ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽግ
ትዕዛዜን ፡ ጠብቅ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖራለህ
ህጌንም ፡ እንደ ፡ ዐይንህ ፡ ብሌን ፡ ጠብቅ
በጣቶችህ ፡ ተሰራቸው ፡ በልብህ ፡ ጽላትም ፡ ጻፋቸው
ጥበብን ፡ አንቺ ፡ እህቴ ፡ ነሽ ፡ በላት
ማስተዋልንም ፡ ወዳጄ ፡ ብለህ ፡ ጥራት

ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቂ
ትዕዛዜንም ፡ በአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽጊ
ትዕዛዜን ፡ ጠብቂ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖሪያለሽ
ህጌንም ፡ እንደ ፡ ዐይንሽ ፡ ብሌን ፡ ጠብቂ
በጣቶችሽ ፡ ተሰራያቸው ፡ በልብሽ ፡ ጽላትም ፡ ጻፊያቸው
ጥበብን ፡ አንቺ ፡ እህቴ ፡ ነሽ ፡ በያት
ማስተዋልንም ፡ ወዳጄ ፡ ብለሽ ፡ ጥራያት

ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ
ጌታ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ (ለእኔ)
ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ
ጌታ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ (ለእኔ)